ለጅሃድ የተሰለፉት ወጣት ሴቶች | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 23.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ለጅሃድ የተሰለፉት ወጣት ሴቶች

በተደጋጋሚና ተራበራ ወጣት ሴቶች የሞቀ ቤታቸዉ እየጣሉ ወደሶርያና ኢራቅ በጦር ፍልሚያዉና እስላማዊ መንግሥት እዚያ አብሮ በማቋቋሙ ሂደት ላይ ራሳቸዉ እንደሚሉት ለመሳተፍ ከአዉሮጳና ከአሜሪካ እየተነሱ መንጎድ ከጀመሩ ጊዜዉ ትንሽ ሰንበት ብሏል።

ሰሞኑን ከሰሜን አሜሪካ ሶስት በአስራ አምስትና በአስራ ሰባት ዓመት መካከል የሚገኙ ኮረዳዎች በጀርመን በኩል አድርገዉ ወደመካከለኛዉ ምሥራቅ ለመሹለክ ሲሞክሩ ፍራንክፈርት አዉሮፕላን ማረፊያ ላይ በፀጥታ አስከባሪ ፖሊሶች ተይዘዋል። ወጣቶቹን እንዲህ ያነሳሳዉ ምንድነዉ? ሃሳቡስ ከየት መጣ የሚሉት ጥያቄዎች ይዞ ጠበብቶችን ያነጋገረዉ የዶቼ ቬለዉ አንድርያስ ጎርዝቭስኪ ያዘጋጀዉን ዘገባ የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለሚካኤል እንደሚከተለዉ አጠናቅሮታል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic