ለዩሮ ቀውስ የወጣው መሪ እቅድ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 06.12.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ለዩሮ ቀውስ የወጣው መሪ እቅድ

የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት በተለይም የዩሮ ተጠቃሚ ሃገራት የዕዳ ቀውስ ያስከተለውን መዘዝ ለመቋቋም የጀመሩት ጥረት ቀጥሏል ።

default

ሜርክልና ሳርኮዚ

ጉዳዩን በዋነኛነት የሚያንቀሳቅሱት ጀርመንና ፈረንሳይ ለችግሩ መከላከያ ይሆናሉ ያሏቸውን እቅዶች አዘጋጅተዋል ። በዚህ እቅድ ውስጥ በጀታቸውን መቆጣጠር የሚሳናቸው የዩሮ ተጠቃሚ አባል ሃገራት ወዲያውኑ ማዕቀብ እንዲጣልባቸው የሚጠይቀው ክፍል ይገኝበታል ። ይህ ተግባራዊ የሚሆነውም የእያንዳንዱ ሃገር የበጀት ጉድለት በህጉ ከተቀመጠው ከአጠቃላዩ የሃገር ውስጥ ምርት ከ 3 ከመቶ ሲበልጥ ነው ። ይህን ህግ የሚተላለፉ አባል ሃገራት ወደ አውሮፓ ህብረት ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ጀርመን አስቀድማ ያቀረበችውን ሃሳብ አንስታ በምትኩ ፍርድ ቤቱ አባል ሃገራት በብሔራዊ ህገ መንግስታቸው ውስጥ ማካተት የሚገባቸውን የተስተካከለ በጀት ደንቦች ከአዲሱ ወይም ከተሻሻለው የአውሮፓ ህብረት ውል ጋር የተጣጣመ መሆን አለመሆኑን የመፈተሽ ሥልጣን እንዲሰጠው ተደርጓል ።ለዩሮ የዕዳ ቀውስ በመፍትሄነት የቀረቡት እቅዶችና የአንዳንዶቹ ጥቅምና ጉዳት የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic