«ለእያንዳንዱ ተማሪ አንድ «ላፕቶፕ» ኮምፒዩተር» | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 08.07.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

«ለእያንዳንዱ ተማሪ አንድ «ላፕቶፕ» ኮምፒዩተር»

በተሰኘው ዓለም አቀፍ ዘመቻ፣ የታዳጊ አገሮች ልጆች፣ ልክ በኢንዱስትሪ እንደበለጸጉት አገሮች፣ እኩዮቻቸው ፣ ከኮምፒዩተር ጋር ተላማምደው እንዲያድጉ በማሰብ የተቋቋመው ድርጅት፣ ኢትዮጵያ ውስጥም ፣ ጅምሩ እንዲከሠት አብቅቷል።

default

«ለእያንዳንዱ ተማሪ አንድ ላፕቶፕ ኮምፒዩተር»በሚል መፈክር ለተጀመረው ዘመቻ፣ የተዘጋጀው ላፕቶፕ፣

በቅድሚያ ከሳይንስ ጋር ግንኙነት ያለው ዜና በጥቂቱ--

ለንደን ፣

ውቅያኖሶች ኮምጣጤነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱና በተቃጠለ አየር (CO2) ክምችት ሳቢያ ሙቀታቸውም ከፍ ማለቱ ፣ በክፍለ-ዓለማት ዐረፍቶች የሚገኘውን የባህር እንስሳትና አትክልቶች ህይወት እስከያዝነው ምዕተ-ዓመት ፍጻሜ ሊያጠፋ ይችላል ሲሉ የሥነ-ፍጥረት ጠበብት ለንደን ላይ በሰጡት መግለጫ ላይ አስጠነቀቁ። ከባቢ አየርን እየበከለ ያለው የተቃጠለ አየር የሚገታበት ጠንከር ያለ እርምጃ ካልተወሰደ፣ መቶ ዓመት አይደለም በ 50 ዓመታት ገደማ ውስጥ እምብዛም ጥልቀት በሌላቸው የውቅያኖስ ጠረፎች፣ የሚገኙ ህይወት ያላቸው ነገሮች ሁሉ እንዳይጠፉ ያሠጋል።

ሐምበርግ፣

የተፈጥሮ አካባቢን ፣ በተለይ ከባቢ አየርን ከብክለት ለመታደግ ፣ በቤንዚን ሳይሆን በሃድሮጂንና ኦክስጂን ጋዝ ኃይል የሚበሩ አኤሮፕላኖችን ማሠማራት እንደሚቻል፣ በዓለም ውስጥ የመጀመሪያ የተባለው በሐምበርግ፣ ጀርመን ፣ የተሠራው አኤሮፕላን አርአያ ነው ተባለ። የሃይድሮጂን ጋዝ ለተፈጥሮ አካባቢ ጠንቅ ባለመሆኑ ለአውቶሞቢሎችም እንዲውል ከታሰበ አያሌ ዓመታት ቢሆንም፣ በታላላቆቹ ኩባንያዎች ዘንድ ዓለም-አቀፍ ስምምነት ላይ ሊደረስ ባለመቻሉ ተግባራዊ ለመሆን አልበቃም።

በሃድሮጂን ጋዝ የሚሽከረከሩ አውቶሞቢሎች እ ጎ አ፣ ከ 2005 ወይም 2030 ዓ ም በፊት ጎዳና ላይ ሊሠማሩ መቻላቸው እንዳጠራጠረ ነው።

ኩዋላ ሉምፑር፣

ማሌሺያ፣ ሂሳብና ሳይንስ ለማስተማር ፣ ከ 6 ዓመት ወዲህ እንደገና ወደራሷ ቋንቋ ማሌይ ለመመለስ በዛሬው ዕለት ወሰነች። ከዚህ ውሳኔ የደረሰችው፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርቱ እንዲሰጥ ማድረጉ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታን ከፍ ለማድረግ ይረዳል ተብሎ የታመነበት ሁኔታ እንደታሰበው ሆኖ ባለመገኘቱ ነው ተብሏል። እቅዱ እንዳልሠመረ ዛሬ ለፓርላማ ያስረዱት ምክትል ጠ/ሚንስትር ሙሂዲን ያሲን ናቸው። ሁሉም የትምህርት ዓይነት በማሌይ ቋንቋ እንዲሰጥ ማድረግ፣ የትምህርቱን ደረጃ ዝቅ ያደርገዋል የሚሉና ይህን አስተሳሰብ የሚቃወሙት ወገኖች ክርክራቸውን አላቋረጡም።

እንግሊዝኛ ለተለያዩ ትምህርቶች መማሪያ ቋንቋ በነበረበት ዘመን፣ መምህራን የአንግሊዝኛ ችሎታቸውን አዳብረው አልተገኙምም ተብሏል። ከ2 ኛ ደረጃ ት/ቤት አስተማሪዎች 19,2 ከመቶ፣ ከአንደኛ ደረጃ ት/ቤትም 9,6 ከመቶው ብቻ ጥሩ የእንግሊዝኛ ችሎታ ያላቸው መሆኑንም ሚንስትሩ አስታውቀዋል። እ ጎ አ ከ 2003 ዓ ም በፊት፣ እንግሊዝኛ እንደ አንድ ቋንቋ የሚማሩት የትምህርት ክፍል ሆኖ ሲቀርብ ሌሎች የትምህርት ዓይነቶች ሁሉ በማሌይ ቋንቋ ነበረ የሚሰጡት። አሁን ተመሳሳይ እርምጃ የሚወሰድ ቢሆም ፣ ምክትል ጠ/ሚንስትር ያሲን ፣ የእንግሊዝኛን እጅግ አስፈላጊነት ፣ መምህራንን በእንግሊዝኛ የማሠልጠኑ ጠቀሜታና ሥነ ጽሑፉንም ይበልጥ የማስፋፋቱን አቅድ አያይዘው ገልጸዋል።

ልዩብሊያና፣

ቶማስ ግራው የተባሉ በርሊን አቅራቢያ ቤርናዉ በተሰኘች ንዑስ ከተማ የሚኖሩ ጀርመናዊ ፣ከኦስትሪያ ጋር በሚያዋስነው የእስሎቬንያ ግዛት፣ የሴኒቸ ከተሰኘችው ከተማ አቅራቢያ፣ ጫካ ውስጥ 2,35 ኪሎግራም የሚመዝን ከስባሪ ኮከብ የተፈረከሰ ንዑስ ድንጋይ(ደንጊያ) ማግኘታቸውን አስታወቁ። ግራው፣ ባለፈው ጥር ወርም፣ የሰሜን ባህር ከፊል በሆነው በምሥራቅ ባህር፣ ከሰማይ የድንጋይ ፍም ሲወነጨፍ ማየታቸውን ከገለጡ በኋላ፣ በመጋቢት ወር አንድ ከኅዋ የተወረወረ ጠጠር ፣ ሎላንድ በተሰኘችው የደንማርክ ደሴት ማግኘታቸውን አስታውቀው እንደነበረ ተጠቅሷል። በእስሎቬንያ የተገኘውን 2,35 ኪሎ ግራም የሚመዝነውን የስባሪ ኮከብ ፍርካሽ ፣ የተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ሳይንቲስቶች ምርምር በማካሄድ፣ ምንጩንና ዕድሜውን ለማወቅ ይጥራሉ ተብሏል።

ሀምበርግ፣

ካለፈው ታኅሳስ 23 ቀን 2001 ዓ ም አንስቶ እስከመጪው ታኅሳስ 2002 በሚዘልቀው በጎርጎሪዮሳውያኑ 2009 የሥነ-ፈለክ መታሰቢያ ዓመት፣ በተጨማሪ የፊታችን ሐምሌ 14 ቀን 2001 ዓ ም፣ የሰው ልጅ ጨረቃ ላይ ያረፈበት 40 ኛ ዓመት የሚዘከር ሲሆን፣ ሰዎች፣ ስለጨረቃ የነበራቸውን ህልምም ሆነ ፣ ወደ ጨረቃ የመጓዝ ምኞታቸውን የሚዳስሱ ልብ ወለድ ታሪኮች፣ ሥዕሎችና የመሳሰሉ በሚቀርቡበት በአሁኑ ወቅት፣ በዚህ ርእስ ዙሪያ የመጀመሪያው ፀሐፊ ማን ነበረ? ለሚለው ጭያቄ መልሱ ፈረንሳዊው Jules Verne ሳይሆን ጀርመናዊው Johannes Kepler ነው የሚለው ሚዛን ሳይደፋ አልቀረም ተባለ። እ ጎ አ ከ 1828-1905 ዓ ም የኖረው Verne በ 1865 ዓ ም፣ «ከምድር ወደ ጨረቃ » በሚል ርእስ ልብ ወለድ መጽሐፍ የደረሰ ሲሆን፣ ከ 1571-1630 ዓ ም የኖረው ኬፕለር፣ በጀርመንኛ ሳይሆን በላቲን ቋንቋ፣ Somnium (የጨረቃ ህልም)በሚል ርእስ በ 1609 ዓ ም ጽፎ ነበር። የታተመው ግን ኬፕለር በሞተ በ 4ኛው ዓመት በ 1634 ዓ ም ነው። ወደ ጀርመንኛ የተተረጎመው በ 1898 ዓ ም ነው። በጨረቃ 32 ኪሎሜትር ስፋት ያለው ሰርጓዳ ቦታ የሚጠራው በኬፕለር ስም ሲሆን፣ ሌላ 2 ኪሎሜትር ስፋት ያለው ሰርጓዳ የጨረቃ አካልም በ Jules Verne ስም ነው የሚጠራው።

ATMO > KEYBORD

ሲመለከቷቸው ደማቅ አረንጓዴ ሆነው የልጆች መጫወቻ ይመስላሉ። ግን የትምህርት ኮምፒውተሮች ናቸው። አላማው እያንዳንዱ በታዳጊ አገር የሚኖር ልጅ አንድ ላፕቶብ እንዲያገኝ ነው።

እ ኢ አ 2005 ነበር ይሄ „one Laptop per Child“ ማለትም አንድ ላፕቶፕ ለአንድ ልጅ ወይም በእንግሊዘኛ ምህፃሩ OLPC የተባለው የግል እርዳታ ድርጅት የተቋቋመው። 5000 የሚሆኑ ላፕቶቦችም ለኢትዮጲያ ትምህርት ቤቶች ተሰተው በአገልግሎት ላይ እየዋሉ ይገኛሉ። እርዳታውን ያቀረቡት አንድ Brescia የተባለች የጣልያን ከተማና እራሱ OLPC ነው። እነዚህ ላፕቶቦች በርዳታ መልክ ከተሰጣቸው ትምህርት ቤቶች አንዱ አዲስ አበባ የሚገኘው ዳግማዊ ሚኒሊክ ት/ቤት ነው።

የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቱ ዲያሬክተር አቶ ሀይሉ አቡራ ለመሆኑ ለስንት ተማሪዎች ላፕቶፑ እንደተሰጠ ለጠየኳቸው ሲመልሱ፦

ድምፅ 1 አቶ ሀይሉ አቡራ

እነዚህ ኮምፒውተሮች ለልጆች ለሸክም እንዳይከብዱ ሆነው የቀረቡ ከመሆናቸም በላይ ለታዳጊ አገሮች ተስማሚ እንዲሆኑ ተደርገው ነው የተሰሩት። ለምሳሌ የኤሌክትሪክ ሀይል ባይኖር እንኳን በፀሀይ ብርሀን እንዲሰሩ ፣ ሀይል ቆጣቢና መፅሀፊያቸው ወይም ኪቦርዱ ውሀ እንዳይገባበት ተደርጎ የተሰሩ ናቸው። የዳግማዊ ሚኒሊክ ተማሪዎችም እቤታቸው ባትሪውን ሞልተው እንደሚመጡ ካለበለዚያም ት/ቤት መሙላት እንደሚችሉ ዲያሬክተሩ ጠቅሰው፦

ድምፅ 2 አቶ ሀይሉ አቡራ

ተማሪዎቹ አሁንም በክረምት ወቅት ላፕቶፑን እቤታቸው መጠቀም ይችላሉ። ኮምፒውሩም ላይ አማርኛና እንግሊዘኛ መፃፍ ይችላሉ። 7ኛና 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ደግሞ አስተማሪዎች የትምህርቱን ፍሬ ሀሳብም ሆነ ዋና ዋና ነጥቦች ወደ ላፕቶፑ ይልኩላቸዋል። ተማሪዎቹም በእጃቸው መፃፍ እንዳይረሱም አልፎ አልፎ መምራት የሚያስረዱትን በደብተራቸው እንደሚፅፉ አቶ ሀይሉ ይገልፃሉ። ለመሆኑ አስተማሪዎቹ በላፕቶፕ ለማስተማር ስልጠና ተደርጓላቸዋል?

ድምፅ 3 አቶ ሀይሉ አቡራ

ይሁንና የዚህን ፕሮጀክት አላማና ሂደት የገመገሙት ከለንደን የመጡት ዴቪድ ሖሎው ምንም እንኳን የፕሮጀክቱ አላማ ጥሩ ቢሆንም በጣም ብዙ ልጆች ኮምፒውተሩን እንደመጫወቻ እንደሚያዩትና በትምህርትም ጊዜ ኮምፒውተሩ ላይ በተገጠመው ካሜራ ፎቶ እያነሱ እንደሚጫወቱ ይገልፃሉ። ኢትዮጲያም ውስጥ ሄደው በ3 ት/ቤቶች በብዛትም አዲስ አበባ በሚገኘው ዳግማዊ ሚኒሊክ እንደቆዩ ይናገራሉ፦

O Ton ሖሎው

«ኮምፒውተሩን ከሚጠቀሙ ልጆች ጋር አውርተናል። አንዳንዶቹ ኮምፒውተሩን እንደወደዱት፤ የትምህርት መፅሀፍ ከመሸከም ላፕቶፕ ይዞ ወደ ት/ቤት መምጣት አስደሳች እንደሆነ ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ ላፕቶፕ ይዞ ወደ ት/ቤት መምጣቱ እንደሚያስፈራቸው፤ ይጠፋብናል ብለው ስለሚያስቡም የመማሪያ መፅሀፍ ይዘው ቢመጡ እንደሚመርጡ ነግረውናል። እና የተለያዩ አስተያየቶች ነው ያገኘነው።»

በመቀጠልም የዚህን ፕሮጀክት በተከታተሉበት ወቅት እንደ ችግር የሚጠቅሱት ካለ ብዬ ላቀረብኩላቸው ጥያቄ፦

O Ton 2 ሖሎው

«ዋናው ያየነው ችግር የመምህራን ስልጠና ጉዳይ ነው። ይኼ የስልጠና ጉዳይ ችግር የሆነበት ምክንያት በክፍል ውስጥ መምህራኑ ላፕቶፖቹን ተጠቅመው ትምህርቱን ስርዐት ለማስያዝ ሲጀምሩ የአስተሳሰብ ለውጥ የግድ ይሆናል። ይሄ ደግሞ ለማንኛውም በአለም ላይ ለሚገኝ አስተማሪ ጊዜ ወሳጅና በቂ ስልጠና የሚጠይቅ ነው። ስለዚህ መምህራኑ ስልጠና እንደሚያገኙ እርገጠኛ ለመሆን ከተቻለ የዚህ ፕሮጀክት ተነሳሽነት ውጤታማ ይሆናል። 2ኛው ችግር ደግም ይዘት ነው ማለትም ተማሪዎቹ በላፕቶፕ አማካኝነት እንዲያገኙ የተፈለገው የስዕራተ ትምህርቱ ይዘት።

እንደሚመስለኝ ይሄ ነው በተገቢ ሁኔታ እየተስተካከለ ያለው። እናም ቡድኑ የመማሪያ መፅሀፍቱንና ለትምህርቱ ሂደት የሚጠቅሙትን በላፕቶፕ ውስጥ እያስገባ ነው።»

ኮምፒውተሮቹ የ 100 $ ላፕቶፕም በመባል ይታወቃሉ። አላማው ኮምፒውተሮችን በትንሽ ዋጋ አምርቶ ለታዳጊ አገሮች በማቅረብ የተማሪዋችዎችን የወደፊት የትምህርት አሰጣጥ ለማሻሻል ታስቦ ነው። እንግዲህ ይህ አላማ እውን ሆኖ ና እናንዳንዱ የኢትዮጲያ ተማሪ የላፕቶፕ ተጠቃሚ በመሆን ትምህርት በአገሪቱ በሙሉ በአፋጣኝ እንደሚስፋፋና እንደሚዳብር ተስፋ እናደርጋለን።

ልደት አበበና ተክሌ የኋላ፣

ነጋሽ መሐመድ