ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት ትብብር | ኢትዮጵያ | DW | 31.12.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት ትብብር

ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢትዮጵያ አሁን ላይ የህልውና አደጋ ውስጥ ናት ብለው በማመን እና ይህንን ችግር ይቀለብሳል ያሉትን አንድ ጠንካራና እውነተኛ የፌዴራሊስቶች ጎራ መፍጠርን አላማ በማድረግ አብሮነት ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት የተባለ ትብብር መፍጠራቸውን አሳወቊ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:13

የፖለቲካ ፓርቲዎች መግባባት

ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢትዮጵያ አሁን ላይ የህልውና አደጋ ውስጥ ናት ብለው በማመን እና ይህንን ችግር ይቀለብሳል ያሉትን አንድ ጠንካራና እውነተኛ የፌዴራሊስቶች ጎራ መፍጠርን አላማ በማድረግ አብሮነት ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት የተባለ ትብብር መፍጠራቸውን አሳወቊ። ፖርቲዎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ እራሳቸውን ለማሰባሰብና ለማጠናከር የሚጥሩ የኮንፌደሬሽን ሃይሎች መኖራቸውንም ጠቅሰዋል። አብሮነት የተባለው ትብብር ህዝባዊ ስብሰባዎችን እንዲሁም ሰላማዊ ሰልፎችንም በጋራ የማድረግ ስምምነት መፍጠሩን ገልጿል። ቀጣዩ ጠቅላላ ሃገራዊ ምርጫ መካሄድ የለበትም ያለድ ይሄው ስብስብ ምርጫው መቼም ይካሄድ መቼም በአንድ የምርጫ ማኒፌስቶ በጋራ ለመወዳደር ፣ ምርጫን ማሸነፍ የሚያስችል ውይይትና ድርድር ከወዲሁ ለመጀመር እንዲሁም ከምርጫ በኋላ የጥምር መንግስት ለማቋቋም አስገዳጅ ሁኔታ ሊፈጠር ስለሚችል በዚህ ዙሪያም ከወዲሁ እየሰራን ነው ብሏም። የስምምነት ፊርማውን ያደረጉት ፖርቲዎች ህብር ኢትዮጵያ ፣ ኢዴፓ እና ኢሃን ናቸው።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

Audios and videos on the topic