ለኢትዮጵያ ጥቃት የኤርትራ ምላሽ | ኢትዮጵያ | DW | 16.03.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ለኢትዮጵያ ጥቃት የኤርትራ ምላሽ

ኤርትራ ከኢትዮጵያ ለተሰነዘረባት ጥቃት አፀፋ ለመመለስ እንደማትሻ አመለከተች። የሐገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሰጡት መግለጫ መንግስታቸዉ የኢትዮጵያ መንግስት ይህን ጥቃት የሰነዘረዉ ከዩናይትድ ስቴትስና ከተመድ የፀጥታዉ ምክር ቤት ድጋፍ

default

ሳያገኝ ነዉ ብሎ እንደማያምንም አስታዉቀዋል። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የሐገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ አሊ አብዶ የጦርነትን አስከፊነት የማያዉቅ ወደጦርነት ያምራ እንጂ ኤርትራ ይበቃታል፤ ለትንኮሳዉ ምልሽ አትሰጥም ብለዋል። ኢትዮጵያ የጥቃት ርምጃ ኤርትራ ላይ መሰንዘሯን መግለጿ ሁለቱ አገሮች ዳግም ወደሌላ ጦርነት ሊገቡ ይሆን ወይ የሚለዉን ስጋት አስነስቷል። ፈረንሳይ ሁለቱም ሐገሮች ለዉይይት እንዲቀመጡ ስትጠይቅ፤ ዩናይትድ ስቴትስ በበኩሏ ኢትዮጵያም ሆነች ኤርትራ አደብ እንዲገዙ ተማፅናለች። ጣሊያንም እንዲሁ ሁለቱ ወገኖች በመካከላቸዉ የተካረረዉን ዉጥረት እንዲያረግቡ አሳስባለች። የአውሮፓው ኅብረት የውጭ ፖለቲካ ኀላፊ ወ/ሮ ካትሪን ኤሽተንም ተመሳሳይ መልእክት ነው በመግለጫቸው ላይ ያስተላለፉት። የአፍሪቃዉን ቀንድ ፖለቲካ የሚከታተሉ ተንታኞች በበኩላቸዉ ለኢትዮጵያ ጥቃት ኤርትራ ወታደራዊ አፀፋ ላትመልስ ትችላለች ባይ ናቸዉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ገበያው ንጉሤ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 16.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14LrR
 • ቀን 16.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14LrR