ለኢትዮጵያውያን ተመላሾች ተጨማሪ በረራ | ኢትዮጵያ | DW | 16.06.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ለኢትዮጵያውያን ተመላሾች ተጨማሪ በረራ

የምህረት ማብቂያው ጊዜ ከረመዳን ጾም የመጨረሻ ሳምንት ጋር መግጠሙ የሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ሊቀመንበርንም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስት የስራ ኃላፊዎችን አሳስቧል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:32

ለኢትዮጵያውያን ተመላሾች ተጨማሪ በረራ

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ህገወጥ ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው እንዲያጓጉዝ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ 17 ሳምንታዊ ተጨማሪ በረራዎችን  ፈቀደ፡፡ 
አስር ቀናት ያህል  የቀረው  የምህረት ማብቂያው ጊዜ ከረመዳን ጾም የመጨረሻ ሳምንት ጋር መግጠሙ  የሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ሊቀመንበርንም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስት የስራ ኃላፊዎችን አሳስቧል፡፡ የረመዳን የጾም ወር የመጨረሻው ሳምንት በመላው ሳዑዲ ዓረቢያ አብዛኞቹ የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ዝግ ይሆናሉ፡፡ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ህጋዊ የስራ እና የመኖሪያ ፍቃድ ለሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች የሰጠው የውጡልኝ ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ የቀሩት ከ 10 ብዙም ያልዘለሉ ቀናት ናቸው፡፡ መውጣት የማይፈልጉት ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ ሆነው መውጣት የሚፈልጉትም በአይሮፕላን እጦት የተነሳ ቁም ስቅላቸውን እያዩ ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የሳዑዲ መንግስት ተጨማሪ አይሮፕላኖች እንዲያርፉ ፍቃድ ያለመስጠቱ ነበር፡፡ አሁን ግን በሳምንት የ17 ተጨማሪ በረራዎች ፍቃድ መገኘቱ ለኢትዮጵያዊያን ተመላሾችም ሆነ ጉዳዩን በዋናነት ለያዙት ሁሉ ታላቅ እፎይታን ሰጥቷል፡፡ አምባሳደር ጊፍቲ አባሲያ በሳዑዲ አረቢያ ዜጎችን በወጉ ለማስመለስ የተቋቋመው ግብረ ኃይል ሰብሳቢ ናቸው፡፡በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ሊቀመንበር አቶ ሻወል ጌታሁን

እንደሚሉት ደግሞ በአሁኑ ወቅት ወደ ሀገር ለመግባት የሚያስችለውን ሰነድ ፈላጊ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ነው ፡፡ መጪው የረመዳን የጾም ወር የመጨረሻው ሳምንት እና ጾሙም ከተፈታ በኋላ የመጀመሪያው ሳምንት የሳዑዲ መንግስት ከፍተኛ የበዓላት ቀን ናቸው በዚህ የተነሳም ዜጎች ከኤምባሲውም ሆነ ከኮሚኒቲው ያገኙትን ያህል አገልግሎት ከሳዑዲዎች ዘንድ ላያገኙ ይችላሉ የሚል ስጋት  እንዳደረባቸው ይገልጻሉ፡፡ ይሁንና በዓዋጁ የመጨረሻ ቀንም ሆነ ከዚያ በሁዋላ ሊከሰቱ ለሚችሉት ሁነቶች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እየተዘጋጀ መሆኑን ያብራራሉ፡፡አምባሳደር ጊፍቲ አባሲያ በበኩላቸው በረመዳን ዝግ ምክምያት በሳዑዲ ዓረቢያ በኩል ለሚፈጠሩ መስተጓጎሎችም ሆነ መዘግየቶች ሀላፊነቱ የራሱ የሳዑዲ መንግስት ነው ይላሉ፡፡ከኤምባሲው የጉዞ ሰነድ የወሰዱት እና ወደ ሀገር የገቡትን ቁጥር በማወዳደር የገቡት በጣም ትንሽ ናቸው ያሉት አምባሳደር ጊፍቲ ለዚህም የመጓጓዣሰነድ ከኤምባሲው ወስደው ወደ ስራ መሰማራት ፣ ከሳዑዲ መንግስት በኩልም የመጨረሻውን የመውጫ ሰነድ ከወሰዱ በኋላ ለሀይምኖታዊ ተግባር ወደ ቅዱሳን ቦታዎች ማምራት ብሎም በሳዑዲ የጸጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ስር መዋል ሰሞኑን ያጋጠሙ ችግሮች መሆናቸውን አብራርተዋል ፡፡ በሀገር ውስጥ ተመላሾችን ለመርዳትም ሆነ ለማቋቋም ሰሞኑን የተደረጉ ጥረቶችን ያነሱት አምባሳደር ጊፍቲ በተለይ በረመዳን ወር መጨረሻ ሙስሊሞች በዘካቸው እነዚህን ወገኖች እንዲያስቡ ጠይቀዋል፡፡

ስለሺ ሽብሩ 

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች