ለአፍሪቃዉያን ባለሙያዎች ዓዉደ ርዕይና ሥልጠና | ኢትዮጵያ | DW | 11.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ለአፍሪቃዉያን ባለሙያዎች ዓዉደ ርዕይና ሥልጠና

በተለያዩ የጋዜጠኝነት ዘርፎች፤ በፎቶግራፍ ማንሳት፤ በፊልም ቀረጻ፤ ተስማሚ በሆነ የትረካ ዘዴ፤ የታሪክ ማስረጃ የሚሆን ጥናታዊ ፊልም አዘገጃጀት ላይ በፈረንሳይ የባህል ማዕከል በአልያንስ ፍራንሴስ ለአንድ ወር የሚዘልቅ ስልጠናና ዓዉደ ርዕይ በመካሄድ ላይ ይገኛል።ትምህርቱን እየሰጡ የሚገኙት ከተለያዩ ሀገሮች የተዉጣጡ አስራ አንድ ከፍተኛ ባለሙያዎች ናቸዉ። ከኢትዮጵያም የዘርፉን ባለሙያዎች ጨምሮ በአጠቃላይ ከአፍሪቃ 250 ሰልጣኞች አዲስ አበባ በተጀመረዉ ስልጠና ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ስልጠናው በተለይ ለሴቶች ትኩረት መሰጠቱ ተመልክቶአል። ይህ ዓዉደ ርዕይ በዓባይ ፊልም እና ቴሌቭዥን አካዳሚ ዳይሬክተር ፣ አቶ አብርኃም ኃይሌ አነሳሽነት ፣ እንዲሁም፣ በተመድ የትምህርት ሳይንስና የባሕል በ«ዩኔስኮ» እና በተለያዩ የምዕራብ ሀገራት ድጋፍ አዘጋጅነት ነው የሚካሄደው። ዝርዝሩን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኋይለጊዮርጊስ

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic