1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ እግር ኳስ ጨዋታ

ዓርብ፣ ሰኔ 7 2016

4 የዓለም እግር ኳስ ዋንጫዎችንና 3 የአውሮጳ እግር ኳስ ዋንጫዎችን ያሸነፈው የጀርመን ብሔራዊ ቡድን በጎርጎሮሳዊው 2014 ብራዚል ውስጥ የተካሄደውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ከወሰደ በኋላ ያጋጠመው ተከታታይ ሽንፈት አብዛኛውን የእግር ኳስ አፍቃሬ አስከፍቷል ።ሆኖም በአሁኑ ጨዋታ የቀድሞውን ስሜት ለመመለስ በቂ ዝግጅት ተደርጓል ይላሉ አሰልጣኙ።

https://p.dw.com/p/4h3Bm
Iserlohn | Italien Fußballnationalmannschaft
ምስል ALBERTO PIZZOLI/AFP/Getty Images

ለአውሮጳ እግር ኳስ ጨዋታ ውድድር የጀርመን ቡዱን ዝግጅት

የዘንድሮው የአውሮጳ እግር ኳስ ጨዋታ በደቡብ ጀርመንዋ በሙኒክ ከተማ ሊጀመር ጥቂት ሰዓታት ቀርተዋል። ዛሬ በውድድሩ መክፈቻ ከስኮትላንድ ጋር የሚጋጠመው የአዘጋጅዋ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን  ከእግር ኳስ አፍቃሪዎች ብዙ ይጠበቅበታል። የቡድኑ አሰልጣኝ ዩልያን ናግልስማን የስኮትላንድ ቡድን ታዋቂ ተጫዋቾች ባይኖሩትም አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል። ሆኖም ቡድናቸን ለጨዋታው ብቁ እና ዝግጁ ነው ብለዋል። በሜዳው የሚጫወተው ቡድናቸው ጫናው ቢበዛበትም እተማመንበታለሁ፤  እንዲያሸንፍም እፈልጋለሁ ሲሉ ምኞታቸውንም ገልጸዋል።

እስከዛሬ ፣ አራት የዓለም እግር ኳስ ዋንጫዎችንና ሦስት የአውሮጳ እግር ኳስ ዋንጫዎችን ያሸነፈው የጀርመን ብሔራዊ ቡድን በጎርጎሮሳዊው 2014 ብራዚል ውስጥ የተካሄደውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ከወሰደ በኋላ ያጋጠመው ተከታታይ ሽንፈት አብዛኛውን የእግር ኳስ አፍቃሪውን አስከፍቷል ።

ዛሬ በሚጀመረው የአውሮጳ እግር ኳስ ጨዋታ የደጋፊዎችን የቀድሞ እጅግ ሞቅ ያለ ድባብ ለመመለስ  ብሔራዊ ቡድኑ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አሰልጣኙ ተናግረዋል። ይልማ ኃይለሚካኤል ከበርሊን ለዘንድሮው ውድድር የጀርመን ቡድን ዝግጅት ምን እንደሚመስል ይቃኛል። 

ይልማ ኃይለሚካኤል
ኂሩት መለሰ