ለኞርዌዩ ነፍሰ ገዳይ የተሰጠው ብይን፤ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 24.08.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ለኞርዌዩ ነፍሰ ገዳይ የተሰጠው ብይን፤

የ 77 ሰዎችን ነፍስ ያጠፋው አንድ የቀኝ ጽንፈኛ ፤ ላይ በዛሬው ዕለት የ21 አመት እሥራት ፈረደ ። ፍርድ ቤቱ በዚሁ ውሳኔው ብሪይቪክ ዐዕምሮው የተነካ ነው ሲልም በይኗል ። ከብይኑ በኋላ የብሬቪክ ጠበቃ ነፍሰ ገዳዩ ንክ ስለተባለ ይግባኝ አይጠይቅም

አንድ የኖርዌይ ፍርድ ቤት ኖርዌይ ውስጥ ከአንድ አመት በፊት የ 77 ሰዎችን ነፍስ ያጠፋው አንድ የቀኝ ጽንፈኛ ፤ ላይ በዛሬው ዕለት የ21 አመት እሥራት ፈረደ ። ፍርድ ቤቱ በዚሁ ውሳኔው ብሪይቪክ ዐዕምሮው የተነካ ነው ሲልም በይኗል ። ከብይኑ በኋላ የብሬቪክ ጠበቃ ነፍሰ ገዳዩ ንክ ስለተባለ ይግባኝ አይጠይቅም ብለዋል ።የ33 አመቱ ቀኝ ፅንፈኛው ብሪይቪክ ዛሬ በንባብ የተሰማውን ብይን በፈገግታ ነበር ያዳመጠው ። ብሬይቪክ 10 ሳምንትት ለወሰደው ችሎት ራሱን እውሮፓን ከሙስሊሞች ወረራ ለመከላከል የሚዋጋ ሰሜነኛ አድርጎ እንደሚያይ ቃሉን ሰጥቷል ። ከግድያው ያመለጡ አንድ አንድ ወጣቶች በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መደሰታቸውን አስታውቀዋል ። የታዛቢዎችም የተጎጂዎችም አስተያየት ምን እንደሆነ የአስክንዲኔቪያውን በተለይም የእሽቶክሆልሙን ዘጋቢአችንን ቴድሮስ ምህረቱን በስልክ ጠይቄው ነበር።

ቴድሮስ ምህረቱ

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic