″ለቀውስ ጊዜ የለንም″ ሚንስትር ነገሪ ሌንጮ | ኢትዮጵያ | DW | 02.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

"ለቀውስ ጊዜ የለንም" ሚንስትር ነገሪ ሌንጮ

በኢትዮጵያ "የኮምዩንኬሽን ቀውስ" መፈጠሩን ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ አስታወቁ። የመንግሥት ኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒሥትሩ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል፣ ውጥረት ነግሷል" የሚሉ አሉታዊ ዘገባዎች ተበራክተዋል ሲሉ ተደምጠዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:01

የዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ጋዜጣዊ መግለጫ

በኢትዮጵያ "የኮምዩንኬሽን ቀውስ" መፈጠሩን ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ አስታወቁ። የመንግሥት ኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒሥትሩ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል፣ ውጥረት ነግሷል" የሚሉ አሉታዊ ዘገባዎች ተበራክተዋል ሲሉ ተደምጠዋል። ዶ/ር ነገሪ "ትክክለኛ ባልሆኑ መረጃዎች የተፈጠሩ ችግሮችን አግዝፎ የቀውስ አጀንዳ ማቀንቀን" በራሱ "ቀውስ" ሆኗል ብለዋል።  ዶክተር ነገሪ "ይኸ ሥራዬ ነው ብለው የሚሰሩ ሚዲያዎች በዝተዋል" ይበሉ እንጂ በስም የጠቀሱት ግን አልነበረም። "ኢትዮጵያን የሚያዋርድ፤ ዜጋን እንደ ዜጋ የማይቆጥር፤ኹከት፣ ጥላቻ እና ክፍፍል የሚሰብክ" ይዘት ያላቸው ገፆች በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን መበራከታቸውንም ጠቁመዋል። "ለቀውስ ጊዜ የለንም" ያሉት ዶ/ር ነገሪ "ሲያጋጥመንም በምክንያታዊነት መፍታት አለብን" ብለዋል። ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ የዛሬውን ጋዜጣዊ መግለጫ ተከታትሎ የሚከተለውን ዘገባ ከአዲስ አበባ ልኮልናል። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሰ
 

Audios and videos on the topic