ለሶማልያ ጸጥታ የኢጋድ ስብሰባ በአዲስ አበባ | ኢትዮጵያ | DW | 25.11.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ለሶማልያ ጸጥታ የኢጋድ ስብሰባ በአዲስ አበባ

ኢትዮጽያ የሶማሊያን ሰላም ለሚያስከብረዉ የአፍሪቃ ህብረት ሰራዊት (AMISOM) ወታደሮች እንደምታዋጣ አስታወቀች።

default

አፍሪቃ ህብረት አርማ

አዲስ አበባ ዛሪ የተሰየመዉ የምስራቅ አፍሪቃ የልማት ባለስልጣን ኢጋድ አባል አገራት የመሪዎች ጉባኤ ኢትዮጽያ ለአፍሪቃ ህብረት ሰራዊት ወታደሮች እንድታዋጣ ጠይቆአታል። አሶሶስየት ፕርስ እንደዘገበዉ ኢትዮጽያ ጥያቄዉን ተቀብላዋለች። ስለምታዋጣዉ የሰራዊት ቁጥር ግን የተዘገበ ነገር የለም። ጉባኤዉ ከዚህም ሌላ ኬንያ ደቡባዊ ሶማሊያ ግዛት ከአክራሪዉ የሶማሊያ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ ጋር የሚዋጋዉን ጦርዋን ከ የአፍሪቃ ህብረት ሰራዊት (AMISOM ) ጋር እንድታዋህድ ጠይቆአል። አንዳንድ ተንታኞች እንደሚሉት በተለይ የኢትዮጽያ ሰራዊት ወደ ሶማልያ መዝመቱ ለአሸባብ ጥሩ የፕሮፓጋንዳ መሳርያ ሊሆን ይችላል።
የአልቃይዳ መንፈስን የያዘዉ የሶማሊያዉ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ ከሶማልያ የሽግግር መንግስት ጋር ደም አፋሻሽ ዉግያን በመክፈት እና በጎረቤት አገራት ሰላምና ጸጥታን መንሳቱ ይታወቃል። ኢትዮጽያ በ1998 አ.ም የያኔዉን የሶማልያ እስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረትን የወጋ ሰራዊት አዝምታ ነበር። ስድስት የምስራቅ አፍሪቃ አገራት የመንግስታት የተሳተፉበት የአዲስ አበባዉ የዛሪ ስብሰባ የኬንያዉ ፕሪዝደንት ሞይኪባኪ የጅቡቲዉ ፕሪዝደንት ኢስማኤል ኡመር ጉሌ እና የሶማልያዉ ፕሪዝደንት ሻሪፍ ሼክ አህመድ ተገኝተዉበታል።

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ