ለሶማልያ ስደተኞች አዲስ መጠለያ ጣብያ በኢትዮጽያ | ኢትዮጵያ | DW | 18.02.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ለሶማልያ ስደተኞች አዲስ መጠለያ ጣብያ በኢትዮጽያ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ተቋም ኢትዮጽያ ዉስጥ አዲስ የሶማልያ ስደተኞች መጠለያ ጣብያ መከፈቱን ከትናንት በስትያ አስታዉቋል።

default

የድርጅቱ የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት (UNHCR) ባወጣዉ መግለጫ በሶማልያ ባለዉ ህዉከት ምክንያት በጎረቤት ኢትዮጽያ በቀን በአማካኝ 200 ያህል ሶማልያዉያን ስደተኞች በመግባት ላይ ናቸዉ። በዚህም ምክንያት ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጽያ Melkadida የተሰኘ ሁለተኛ የስደተኞች መጠለያ ተቋሙ መክፈቱን አስታዉቋል። በኢትዮጽያ ዉስጥ ባጠቃላይ አምስት የስደተኞች ጣብያ እንዳለ እና 125 ሺህ ስደተኞች እንሚኖሩ ተጠቅሶአል። ይህንን ተገባ በተመለከተ አዜብ ታደሰ በኢትዮጽያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊን አነጋግራ ዘገባ ይዛለች።

አዜብ ታደሰ፣

አርያም ተክሌ