ለስደተኞች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በጀርመን | ኤኮኖሚ | DW | 09.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

ለስደተኞች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በጀርመን

በቅርቡ ደግሞ የኮምፕዩተር ጠበበት ወጣት ሥራ አጥ ስደተኞችን በኮምፕዩተር አሠልጥነው በሥራ ዓለም እንዲሰማሩ በማገዝ ላይ ናቸው ። ከዋና ከተማዋ ከበርሊን የመጣው ይህ ሃሳብ በኮሎኝ ከተማም ተግባራዊ ሆኗል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:24
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
09:24 ደቂቃ

ለስደተኞች የበጎ ፈቃድ አገልግሎትከቅርብ ወራት ወዲህ ጀርመን ለገቡ በርካታ ስደተኞች ጀርመናውያን ልዩ ልዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ናቸው ። የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስደተኞችን ያስተምራሉ ፣ ሀኪሞችና ነርሶች የነፃ ህክምና አገልግሎት ይሰጣሉ ። ከፊሉ ባዶ ቤቱን ለቆላቸዋል ፣ ጡረታ የወጡ አስተማሪዎችም እውቃታቸውን በፈቃደኝነት እያጋሩ ነው ። እነዚህ ሁሉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የሚከናወኑት ያለ መንግሥት እገዛ ነው ። በቅርቡ ደግሞ የኮምፕዩተር ጠበበት ወጣት ሥራ አጥ ስደተኞችን በኮምፕዩተር አሠልጥነው በሥራ ዓለም እንዲሰማሩ በማገዝ ላይ ናቸው ። ከዋና ከተማዋ በርሊን የመጣው ይህ ሃሳብ በኮሎኝ ከተማም ተግባራዊ ሆኗል ። የዛሬው ከኤኮኖሚው ዓለም ትኩረት ነው የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል አዘጋጅቶታል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic