ለስደተኞች ቤት ፍለጋ በጀርመን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 20.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ለስደተኞች ቤት ፍለጋ በጀርመን

በአጭር ጊዜ ውስጥ እዚህ ጀርመን ለገቡ ስደተኞች ሁሉ መኖሪያ ቤት ባለመገኘቱ፤ አሁን ድረስ በርካታ ስደተኞች በየዱንኳኑ ውስጥ ተጠልለዉ ይገኛሉ። የስደተኞቹን የድንኳን ኑሮ አስከፊ የሚያደርገው ደግሞ ክረምት እየገባ መሆኑና ቅዝቃዜውን በድንኳን መወጣት አዳጋች ማድረጉ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ እንደ በርንድ ኒስን ያሉ የመንግሥት መኖርያ ቤቶችን የተከራዩ ጀርመናውያን ቤታችሁን ለስደተኞች መኖርያ ስለምንፈልገው፤ ለቃችሁ እንድትወጡ እና ቁልፍ እንድታስረክቡ የሚል የስንብት ደብዳቤ ደርሷቸዋል። ይህንን ለመገናኛ ብዙኃን ይፋ ያደረጉት የቤት ተከራይ ታሪክ፤ ጥላቻ እና ዘረኝነት በመጤ እና በኖዋሪዎቹ ዘንድ ምን ያህል በቀላሉ ሊፈጥር እንደሚችል ያመላክታል። አንዳንድ ተከራዮች ለቀን አንወጣም በማለት አድማ ሲመቱ ሌሎች ጉዳዩን ለጠበቃ ሰጥተዋል።

ናስታስያ እሽትራሁለር / ይልማ ኃይለሚካኤል

ልደት አበበ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic