ለማርስ ጉዞ፣ የዝግጅት መፈተሻ ምርምር፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 01.04.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

ለማርስ ጉዞ፣ የዝግጅት መፈተሻ ምርምር፣

ምድራችን ፣ የብሱና ውቅያኖሱ፣ ተራራውና መስኩ፣ ከባቢ አየራችንም ጭምር ከሰው- ሠራሽ ብክለት እንዲተርፍ፣ ነጋ-ጠባ ማሳሰቢያም ሆነ ውትወታ ማቅረቡ እንዳልተጓደለ የታወቀ ጉዳይ ነው።

default

ሞስኮ ውስጥ፣ ለማርስ ጉዞ ዝግጅት መፈተሻ፣ ለ 105 ቀናት ቱቦ ከሚመስል ምርምር ማካሄጃ ቤት ውስጥ ከገቡት 4 ሩሲያውያንና አንድ ፈረንሳዊ ከሚገኙበት ቡድን ጋር ከ 5,600 አመልካቾች መካከል ተመርጦ የተቀላቀለው የ 28 ዓመቱ ወጣት ጀርመናዊ፣ ሻምበል ኦሊቨር ክኒከል፣

ባለፈው ሳምንትም፣ ኅዋ፣ የቁሻሻ(የብረታ-ብረት ስብርባሪ መጣያም ሆነ ማከማቻ እንዳይሆን)ያለውን ሥጋት አስመልክተን መዘገባችን የሚታወስ ነው። ፕላኔታችን፣ በሰው-ሠራሽና በተፈጥሮ፣ ተፈታታኝ አደጋ ሊያጋጥማት እንደሚችልe እየታወቀም ህይወትን መደገፍ ይቻሉ-አይቻሉ፣ በውል ያልታወቀላቸውን ዓለማት ለማሰስ ዝግጅቱ ጋብ ያለ አይመስልም። ምድራችን፣ ከኅዋ፣ በሰው-ሠራሽና በስብርባሪ ከዋክብት የሚደቀንባትን አደጋ ለመግታት ዘላቂ ብልሃት የተገኘም አይመስልም።

Mars Lander የተባለችው መንኮራኩር ፣ ከአያሌ ወራት በፊት ስለማርስ ላቅ ያለ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ መረጃዎች ካቀረበች ወዲህ፣ ስለሌሎች በተለይ ከምድር ጋር ተመሳሳይ ባህርይ ይኖራቸዋል ተብለው የሚታሰቡ ፕላኔቶችን ይበልጥ ማወቅ ይቻል ዘንድ ጠጋ አድርጎ የሚያሳይ «ኬፕለር» የተባለው 600 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበትና ቢያንስ 3 ዓመት ተኩል ተግባሩን የሚያካሂድ፣ ቴሌስኮፕ ከአንድ ወር ገደማ በፊት መላኩ ይታወሳል።

በትናንቱ ዕለት ደግሞ፣ በማርስ ላይ ትኩረት ያደረጉት ዓለም አቀፍ የምርምር ተቋማት ሞስኮ ውስጥ 105 ቀናት የሚወስድ ፣ ወደማርስ የሚላኩ ሰዎች በረጅም ጊዜ ጉዞ፣ ምን ሊያጋጥማቸው እንደሚችልና ከወዲሁም መፍትኄውን መሻት ይቻል ዘንድ ይረዳል ተብሎ የታመነበትን ሙከራ ጀምረዋል። ማርስ ድርሶ ለመመለስ፣ በአሁኖቹ የጠፈር መንኮራኩሮች ፍጥነት ፣ አንድ ዓመት ከ 155 ቀናት እንደሚወስድ እሙን ነው።

ተክሌ የኋላ፣

ነጋሽ መሐመድ፣