ለሌላ ሀገር የሚሮጡ አትሌቶች | ስፖርት | DW | 16.08.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

ለሌላ ሀገር የሚሮጡ አትሌቶች

ዜግነታቸዉን ቀይረዉ ለሌላ ሀገር የሚሮጡ አትሌቶችን በታላላቅ የዉድድር መድረኮች ላይ መመልከት አዲስ መሆኑ ቀርቷል። ከዚህ ቀደም በዚሁ ጉዳይ ጎልተዉ ይታዩ የነበሩ ኬንያዉያን አትሌቶች ተራዉን ለኢትዮጵያዉያኑ የለቀቁ ይመስላሉ።

በተለይም በሞስኮ በመካሄድ ላይ በሚገኘዉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዜግነታቸዉን የቀየሩና በሌሎች ሀገራት ሰንደቅ ዓላማ ስር የሚወዳደሩ ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች ቁጥር ከመቼዉም ጊዜ ይበልጥ ከፍተኛዉን ቁጥር መያዙን ትገልጻለች በስፍራዉ የምትገኘዉ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ። እናም ትላለች ሃይማኖት ለአትሌቶቹ ፍልሰት በርካታ ምክንያት ቢጠቀስም ጉዳዩ ግን አሳሳቢ መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል። በሌላ በኩልም በርካታ ተፎካካሪ አትሌቶች ላሉዋት ሀገር በታላላቅ ዉድድር ለመካፈል ሌሎች አማራጮችን መጠቀም አለባቸዉ የሚሉ ወገኖችም መኖራቸዉን ትገልጻለች። ለዝርዝሩ ሃይማኖት

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic