ለሁለቱ የኢትዮጵያ ሲኖዶሶች አዲስ አስታራቂ ኮሚቴ | ኢትዮጵያ | DW | 01.12.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ለሁለቱ የኢትዮጵያ ሲኖዶሶች አዲስ አስታራቂ ኮሚቴ

ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ጥረት ተሞክሮ መክሸፉ የሚታወስ ቢሆንም፤ አሁን አዲስ ጥረት መጀመሩን የሚገልፀዉ አስታራቂ ኮሚቴ ሚናው ሽምግልና እንደሆነ እና አላማዉም ሁለቱን ሲኖዶሶች አንድ ማድረግ መሆኑን አስታውቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:56

የኮሚቴው ሚና ሽምግልና ዓላማው ደግሞ ሁለቱን ሲኖዶሶች አንድ ማድረግ ነው ተብሏል።

የሀገር ውስጥ እና ስደተኛው በሚል ተለያይተው ለዓመታት የዘለቁትን የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለማስታረቅ የሚሰራ አዲስ ኮሚቴ ተቋቋመ። አዲስ የተቋቋመው ይኽው ኮሚቴ በሀገር ውስጥ ካለው የቤተክርስቲያኒቱ ሲኖዶስ እና በዉጭ ሀገር በስደት ከሚገኘዉ ሲኖዶስ ድጋፍ እንዳለው የኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ጥረት ተሞክሮ መክሸፉ የሚታወስ ቢሆንም፤ አሁን አዲስ ጥረት መጀመሩን የሚገልፀዉ አስታራቂ ኮሚቴ ሚናው ሽምግልና እንደሆነ እና አላማዉም ሁለቱን ሲኖዶሶች አንድ ማድረግ መሆኑን አስታውቋል። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል። 
መክብብ ሸዋ 
ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ
 

Audios and videos on the topic