ሆሳዕና በአል አከባበር / አዲስ የፊልም ፊስቲቫል | ባህል | DW | 28.03.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ሆሳዕና በአል አከባበር / አዲስ የፊልም ፊስቲቫል

እንኳን ለሆሳዕና በአል አደረሳችሁ ይላል የለቱ የባህል መድረክ ዝግጅታችን፣ የሆሳዕና በአል በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በአገራችን በደማቅ ሁኔታ ይከበራል

default

በየእሩሳሌም የሆሳዕና በአል አከባበር

በተለይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በአሉን በደመቀ ሁኔታ ታከብራለች፣ የለቱ መድረካችን የሚዳስሰዉ ርእሱ ነዉ፣ የሆሳዕና ሃይማኖታዊ በአል፣ ወጉን እና ያከባበሩን ሁኔታ በጥቂቱ ካነሳን በኋላ፣ ባለፈዉ አርብ በአገራችን በኢትዮጽያ የተከፈተዉን አራተኛዉን አዲስ አለም አቀፍ የፊልም ፊስቲቫልን እንቃኛለን
እዚህ በጀርመን የብዙሃን መገናኛ እና ድረ-ገጾች በያዝነዉ ሳምንንት መገባደጃ ላይ ኢትዮጽያዉያን የሚከተሉት ልዩ የቀን ቀመር የፋሲካ በአላቸዉ ዘንድሮ ከአዉሮጻዉያኑ የፋሲካ ክብረ በአል ጋር አንድ ላይ ይዉላል ሲሉ በደማቁ ጽፈዉታል። በዚሁ ርእስ አንቀጽ ስር ኢትዮጽያዉያን የኦርቶዶክስ እምነትን የሚከተሉ ኢትዮጽያዉያን ሃምሳ አምስት ቀን ጾመዉ ፋሲካን ሲያከብሩ በደስታ እና በደማቅ ሁኔታ ነዉ። በበአሉ ህጻናት እርጥብ አረንዴ ጉዝጓዝ ይነሰንሳሉ፣ ቤተሰቦች ጥሩ ምግብን በማዘጋጀት ይገባበዛሉ፤ ሲል በዝርዝር አስቀምጦታል፣ በአገራችን የፋሲካ በአል ከመድረሱ አንድ ሳምንት ሲቀረዉ በሚከበረዉ በሆሳእና በአል በዘንባባ ዝንጣፊ የተለያዪ ጌጣጌጦችን በማድረግ ህጻናት አዋቁ ሲያከብረዉ ይታያል። የሆሳዕና በአል ምንን በማስመልከት ይከበራል። በበርሊን በኢትዮጽያዉያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ ይገልጹልናል! ያድምጡ
አዜብ ታደሰ