1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ አሙሩ፤ አጋምሳ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ዳግም ስራ መጀመራቸው ተገለጸ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 2 2016

ለረዥም ጊዜ በጸጥታ ችግር ውስጥ በቆየው የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ አጋምሳ ከተማ ውስጥ ከ3 ዓመት በኃላ ባንክ ስራ መጀመሩን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በአካባቢው የጸጥታ ሁኔታ መሻሻሉ ቢገለጽም ወደ አጎራባች ወረዳ እና ዞን አስተዳዳር የሚወስደው የመጓጓዣ አገልግሎት ግን እስካሁን አለመጀመሩን ነዋሪዎችቹና የከተማዋ ከንቲባ ተናግረዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4jFsV
Infografik GRAPHIC Karte Amuru Woreda, Äthiopien
ምስል DW

ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ አጋምሳ ከተማ የባንክ አገልግሎት ተመለሰ

በአሙሩ ወረዳ አጋምሳ ከተማ  አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ዳግም ስራ ጀምረዋል

ለረዥም ጊዜ በጸጥታ ችግር ውስጥ በቆየው የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ አጋምሳ ከተማ ውስጥ ከ3 ዓመት በኃላ የባንክ አገልግሎት መጀመሩን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡  በአካባቢው የጸጥታ ሁኔታ መሻሻሉ ቢገለጽም ወደ አጎራባች ወረዳ እና ዞን አስተዳዳር የሚወስደው የመጓጓዣ አገልግሎት ግን እስካሁን አለመጀመሩን ነዋሪዎችቹና የከተማዋ ከንቲባ ተናግረዋል፡፡ በከተማዋ የወባ በሽታ ስርጭትም ብርቱ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡

 በኦሮሚያ ግጭት በተባባሰባቸው አከባቢዎች የተፈተነው የጤና አገልግሎት

ከነሐሴ 2014 ዓ.ም አንስቶ የባንክ አገልግሎት ሙሉ በመሉ ተቋርጦ ቆይቷል፡፡

ከሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አስተዳደር መቀመጫ ከሆነው ሻምቡ ከተማ በ94 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚትገኘዋ የአሙሩ ወረዳ አጋምሳ ከተማ ባለፉት ዓመታት በቆየው ጸጥታ ችግር ሳቢያ የጤና፣ባንክና ልዩ ልዩ ተቋማት አገልግሎት በሙሉና በከፊል ተቋርጦ መቆየቱን ያነጋርናቸው ነዋሪዎች አስታውቋል፡፡ በተለይም   በነሐሴ 2014 ዓ.ም የታጠቁ ሐይሎች ወደ ከተማዋ በመዝለቅ ባደረሱት ጥቃት ከፍተኛ ውድመት ደርሶ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው ተቋርጦ የቆው የባንክ አገልግሎትም  ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ ወደ ስራ መግባቱን ምትኩ ገመቹ የተባሉ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለዶይቼቨለ ተናግረዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሁለት ወረዳዎች በግጭት ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖሩ ተናገሩ

በአሙሩ ወረዳ አጋምሳ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድብ ባንክ በትናንትናው ዕለት ዳግም መከፈቱን ሌላው የከተማው ነዋሪ በስልክ ተናግረዋል፡፡ ከማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ቋማት  እጦት በተጨማሪም በከተማው ዙሪያ ከሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች  ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በጸጥታ ችግር ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለው እንደነበርም ገልጸዋል፡፡ በዚሁ ምክንያት አርሶ አደሩ ከ2 ዓመት በላይ ባለማረሱ በምግብ እጥረት ምክንያት የወባ በሽታ በአካባቢው ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የአሙሩ ወረዳ ተፈናቃዮች ሮሮ

ሁለት ባንኮች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል

በአሙሩ ወረዳ የአጋምሳ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ ጌታሁን ደሳለው በከተማው አምስት ከሚደርሱት ባንኮች መካከል 2ቱ በትናንትናው ዕለት ወደ ስራ መግባታቸውን አመልክተዋል፡፡ ከ36ሺ በላይ ሰዎች የሚኖሩባት አጋምሳ ከተማ ከነሐሴ 24/2014 ዓ.ም ጀምሮ የባንክ አገልግሎት መሉ በመሉ ተቋርጦ እንደነበርም ከንቲባው ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ወደ ተለያዩ ወረዳዎችና አጎራባች ከተሞች ጋር የሚያገናኙ የትራንስፖርት አገልግሎቶች ተቋርጦ እንደሚገኙም አመብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ገንዘብ
በአሙሩ ወረዳ የአጋምሳ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ ጌታሁን ደሳለው በከተማው አምስት ከሚደርሱት ባንኮች መካከል 2ቱ በትናንትናው ዕለት ወደ ስራ መግባታቸውን አመልክተዋል፡፡ ምስል MICHELE SPATARI/AFP

የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ተፈናቃዮች ሰብአዊ ድጋፍ አለማግኘታቸው

‹‹ ነሐሴ 23/24/2014 ዓ.ም በታጠቁ ሐይሎች የህዝብ ብ ተዘርፈዋል፡፡ በከተማው ላይ ጉዳት ደርሶበት ነበር፡፡ በከተማው ውስጥ የነበሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ሲንቄ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ተዘርፎዋል፡፡ ከዛ ወዲህ 3 ዓመታት አስቆጥረዋል ማለት ነው፡፡ ህብረተሰቡ ምንም አይነት አገልግሎት አጥቶ በጣም እየተቸገረ ነበር፡፡ መንገድም ተዘግቶ ነበር፡፡ እስከ ሻምቡ በዚህም ወደ ምስራቅ ወለጋ ጊዳ ወረዳ ዝግ ነው ማለት ነው፡፡ ከ3 ዓመታት በኃላ  ትናንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ሲንቄ ባንክ ስራ ጀምሯል፡፡‹‹

አሙሩ ወረዳ በተደጋጋሚ በደረሰበት ጥቃት ከተለያዩ ገጠራማ አካባቢዎች ተፈናቅለው የነበሩ ከ40ሺ በላይ ሰዎች ለ2 ዓመታት በአጋምሳ እና ኦቦራ በተባሉ ከሞች ተጠልሎ እንደነበር ወረዳው ገልጸዋል፡፡ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የነበሩ 45ሺ 915 ዜጎች በግንቦት 2016 ዓ.ም ወደ ቤታቸው መመለሱን የወረዳው የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት/ ቡሳ ጎኖፋ  መግለጹ ይታወሳል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ 

ታምራት ዲንሳ

ሸዋዬ ለገሰ