ህገ ወጥ የገንዘብ ፍሰትና ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 01.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ህገ ወጥ የገንዘብ ፍሰትና ኢትዮጵያ

ባለፉት 5 ዓመታት ኢትዮጵያ በህገ ወጥ የገንዘብ ፍሰት ያጣችው ገንዘብ መጠን 10 ቢሊዮን ዶላር ይገመታል ። ኢትዮጵያም አጣች የተባለው ገንዘብ በሃገሪቱ ድህነትን ለመቀነስ የተወሰዱትን እርምጃዎች ሊያፋጥን ይችል እንደነበርም ነው የተገለፀው ።


አፍሪቃ በህገ ወጥ የገንዘብ ፍሰት በየዓመቱ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደምታጣ የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት የሚያወጧቸው ዘገባዎች ያስረዳሉ ። ቅርብ ጊዜ ይፋ የተደረገው የአፍሪቃ ህብረትና የኣፍሪቃ ኤኮኖሚክ ኮሚሽን በጋራ አስጠንተው ያወጡት ዘገባ ክፍለ ዓለሚቱ ባለፉት 50 ዓመታት በህገ ወጥ የገንዘብ ፍሰት 1 ትሪሊዮን ዶላር እንደቀረባት አስታውቋል ። ከአፍሪቃ በዚህ ጊዜ የባከነው ገንዘብ መጠን ክፍለ ዓለሚቱ በዚሁ ጊዜ ውስጥ ካገኘችው የልማት እርዳታ ጋር ተቀራራቢ መሆኑን ጥናቱ ያስረዳል ።በጥናቱ መሠረት ከአፍሪቃ ህጋዊ ባልሆነ የገንዘብ ፍሰት በዋነኛነት ከሚጠቀሱ 10 የአፍሪቃ ሃገራት ውስጥ ኢትዮጵያ ትገኝበታለች ። በዚሁ ጥናት እንደተመለከተው ባለፉት 5 ዓመታት ኢትዮጵያ በህገ ወጥ የገንዘብ ፍሰት ያጣችው ገንዘብ መጠን 10 ቢሊዮን ዶላር ይገመታል ። ኢትዮጵያም አጣች የተባለው ገንዘብ በሃገሪቱ ድህነትን ለመቀነስ የተወሰዱትን እርምጃዎች ሊያፋጥን ይችል እንደነበርም ነው የተገለፀው ። ከፍተኛ የውጭ እርዳታና ብድር በምታገኘው በኢትዮጵያ ህገ ወጥ የገንዘብ ፍሰት ያደረሰው ጉዳት እንዴት ይገመገማል ? መከላከያውስ ምንድነው ? ህገ ወጥ የገንዘብ ፍሰትና ኢትዮጵያ የዛሬው እንወያይ ርዕስ ነው።

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic