ሃያኛዉ ዓመት የጀርመን ዉሕደት-ከሃያ አመት በሕዋላ I | ይዘት | DW | 01.10.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ይዘት

ሃያኛዉ ዓመት የጀርመን ዉሕደት-ከሃያ አመት በሕዋላ I

የወጣቶች ማሕበራዊ ጉዳይ ተመራማሪዉ ቶማስ ጌንሲከ እንደሚለዉ በምስራቅ የሚታየዉ የቀኝ አክራሪ ህዝብ እንደ ምዕራቡ ሁሉ በቁጥር አነስተኛ ነዉ። የምስራቅ ጀርመን ወጣቶች ከምዕራቦቹ ይልቅ የፖለቲካ፥ የኢኮነሚ እና የማህበረሳባዊ ጉዳዮችን በማንሳት ከጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ ጋር ያነጻጽ

default

የኮሎኙ ወጣት ማቲዮ ብሮስተ

ከየመቶዉ-የጀርመናዊ ሃያዉ ጀርመንን የሚያቃት ዳግም አንድ ሆና እንጂ ለሁለት ተከፍላ አያዉቃትም። እነዚህ ሁሉ ዜጎች የተወለዱት ከጎርጎሮሳዉያኑ 1990አ.ም በኋላ ነዉ።ታድያ ስለጀርመን ዉህደት ምን ያስባሉ? ምን ያዉቃሉ? ከ1990 በኋላ የተወለደዉ ትዉልድስ አንድነትን ያዉቃል?

ጀርነመናዊዉ ወጣት ማቴዎ ብሮስቴ ጠዋት ተነስቶ፥ ገላዉን ታጥቦ እና ትኩስ ቡናዉን ፉት ብሎ ከቤቱ እንደወጣ የትምህርት ቤቱ የጠዋት ደወል ያቃጭላል። ማቴዎ ከሚማርበት ኤርምጋርዲስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ቤቱ ድረስ ሃያ ሜትር ያህል ብቻ ነዉ የሚርቀዉ። ኤርምጋርዲስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ በኮለኝ ከተማ ባየንታል በሚባለዉ ሠፈር ደቡባዊ ክፍለ ከተማ ይገኛል።

St. Irmgardis Gymnasium Köln

የኮሎኙ የኢርም ጋዲስ ት/ቤት

የጀርመን ዉሕደት ለተማሪዎቹ ታሪክ ነዉ
መምህርት ፔትራ ሊንስ በዚህ ትምህርት ቤት ዉስጥ የታሪክ አስተማሪ ናት። ዛሬ ልታስተምር የተዘጋጀችበት ርዕስ ስለ አዲስትዋ ጀርመን የቆየ ታሪክ ነዉ።«የበርሊኑን ግንብ ያየ አለ?» የዛሬ ክፍለ-ጊዜዋን በጥያቄ ጀመረች። በክፍል ዉስጥ ከሚገኙት ተናማሪዎች መካከል ሶስት አራተኛዉ የበርለሊንን ግንብ አይተዉት እንደ ነበር መልሰዉላታል። በምዕራብ ጀርመን አኳያ የሚገኘዉ በርሊንን ለሁለት የከፈለዉ ግንብ በስእል እና በቀለም ያሸበረቀ እንደነበር በመግለጽ፣ መምሕሯ በምስራቅ አኳያ የነበረዉ ግንብ እንዴት ሊመስል እንደሚችል ጥያቄ ታቀርባለች። አንድ ተማሪ « ምንም ነገር አልነበረም » ምንም አይነት ስእል ካልተሳለበት ምንም ካልነበረበት ለምን እንዳልነበረ ደግማ ትጠይቃለች። «በምስራቁ አኳያ ማንም ሰዉ ግንቡን እንዲጠጋ ፈቃድ አልነበረም» ሲል ሌላዉ ተማሪ ይመልሳል። ትክክል «በግንቡ አካባቢ ለመጠበቅያ እንዲሆን የተዘረጋ ለህይወት አደገኛ የሆነ የኤሌትሪክ ሽቦ እንዲሁም የመጠበቅያ ማማ በመኖሩ ነዉ» ስትል መምህርት ፔትራ በማከል ታስረዳለች።

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጀርመንን መዋሃድ ታሪክ በተለይ የ 17 እና 18አመት ወጣቶች በፊልም ነዉ የሚዉቁት። ግልጽም የሆነላቸዉ አንድ መሆንዋ ነዉ። አንድ ተማሪ « መዋሃድዋ ብቻ ሳይሆን በልባችን በሃሳባችንም ቢሆን የቀረ የሚነጣጥል ግንብ የለም፣ ይህ ትዉልድ ባለበት ጊዜ ነዉ ተወልጄ ያደኩት» ሲል ይመልሳል። ሌላዉ ጓደኛዉም ይህንኑ ሃሳብ በመደገፍ በአዎታ

Matteo und Carla Brossette

ማቴዎና ካርላ

ጭንቅላቱን ይነቀንቃል።

ምንም ልዩነት አይታይም
በባቫርያ ግዛት በሙንሽን በሚገኘዉ እና TNS በሚል ምሕፃረ-ቃል በሚጠራዉ የማህበራዊ ጉዳይ ጉዳይ ጥናት ተቋም የማህበራዊ ኑሮ ባለሙያዉ ቶማስ ጌንሴክ «ጀርመን ከተዋሃደች ከሃያ አመት በኋላ በምስራቅም ሆነ በምዕራብ የሚኖሩት ወጣቶች ልዩነት አይታይባቸዉም» ሲሉ በወጣቶች ላይ ያደረጉትን ጥናት ይፋ አድርገዋል። በገንዘብ አኳያ በምዕራብ ያሉ ወጣቶች በምስራቅ ከሚኖሩት በለጥ ብለዉ ስለሚታዩ፥ በምስራቅ የሚኖሩት አቻዎቻቸዉ የወደፊት ህይወትን ለመገንባት በሚያደርጉት ትግል በምዕራብ ከሚገኙት አነስ ብለዉ ወይም የወዲት እጣቸዉን በጥርጣሪ ሲመለከቱት ይስተዋላል። ይህ ደግሞ የማያስገርም እንደሆነ የማህበራዊ ጥናት አዋቂዉ ቶማስ ጌንሴክ ይገልጻሉ። ምክንያቱም «በምስራቅ ጀርመን የወጣት የስራ አጥ ቁጥር ከምዕራቡ በእጥፍ ይገኛልና»
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዉ ማቴዎ ቤተሰቦቹ ጥሩ ገቢ ስላላቸዉ የመማርያ ቁሳቁስ ችግር የለበትም። በዚህም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኳላ የከፍተኛ ትምህርቱን በቅየሳ ሞያ አጠናቆ ስጳኝ ዋና ከተማ ማድሪድ ለመኖር ነዉ ምኞቱ።


የሁሉም ትኩረት ወደ ሙዚቃ ነዉ
ከቀትር በኋላ ነዉ።ጆሴፊነ እና አንዲት ጓደኛዋ ማቴዎስ እራሱ በሰራዉ አንድ የሙዚቃ ስቱዲዎ ዉስጥ ናቸዉ። ጆሴፊነ አንድ ሙዚቃ ታዜምለታለች።ማቴዎ የኮለኝ የሙዚቃ ጓድ አባል ነዉ። በዚህ ስቱዲዎ ዉስጥ ሙዚቃን ይጽፋል፣ ያትማልም።ስቱዲዎዉ ሙዚቃ መቀመርያ፣ ማጫወቻና ማቀናበሪያ ኮንፒዉተር በሙሉ አሟልቶ ይዟል።

Matteo und Josephine

የማቴዮ ጓደኞች ስቱዲዉን ይጎብኙለታል

ማቴዎስ ፖለቲካን በጥቂቱ ቢያዉቅም በፖለቲካ ጉዳይ አይሳተፍም። ሙዚቃ ባንፃሩ ሕይወቱ ነዉ። በቅርቡ በምስራቅ ጀርመን በምትገኘዉ በላይፕሲግ ከተማ አንድ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ተገኝቶ የምስራቅ ጀርመን ወጣት ፖለቲካን ትኩረት ዉስጥ እንደሚያስገባ አሳይቶታል። «በርካታ ወጣቶች ቀኝ አክራሪን የሚቃወም፣ አልያም «ከጦርነት ፍቅር» የሚል ቲሸርት አጥልቀዉ ነበር በሙዚቃ ድግሱ ላይ የተገኙት። «እዚህ እኛ ጋ» ይላል «ማለት በምዕራብ ጀርመን» ይህ አይነት ነገር የሚታየዉ ሰላማዊ ሰልፍ ሲኖር ብቻ ነዉ። በምስራቅ ግን ፖለቲካን የሚያንጸባርቅ ቲሸርት አድርገዉ ሲዘዋወሩ ማየቱ የተለመደ ነዉ።ስለዚህም በምስራቅ ያለዉ ነዋሪ የፖለቲካ አቋሙን በግልፅ ያሳያል ማለት ነዉ።» በማለት ትዝብቱን ይገልፃል።

ጆሴፊንም ብትሆንም በሌላ አጋጣሚ ተመሳሳይ አስገራሚ ነገር አጋጥሞታል።ምስራቅ ጀርመን ሜክልቡርግ ፎርፖመርን ክፍለ-ግዛት በዩዞዶም በተሰኘችዉ አነስተኛ የገጠር ከተማ ዉስጥ አንድ ቀኝ አክራሪ የሙዚቃ ባንድ የሚያዜመዉን ሙዚቃ በማየትዋ መደንገጥዋን እና መገረሟን ትገልጻለች። የሙዚቃ ባንዱ ቀኝ አክራሪዎችን የሚያወድስ ሙዚቃ በማዜሙ ታዋቂ መሆኑን እንዲሁም የከተማይቱ ነዋሪዎች ይህን የሙዚቃ ባንድ በመደገፍ ቀኝ አክራሪን የሚያወድስ አርማ ያለበትን ቲሸርት አድርገዉ ጎዳና መዉጣታቸዉን ማየትዋ እጅግ አሳፋሪ መሆኑን ተናግራለች።

ለምዕራብ ጀርመን ወጣቶች የጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ ሥርዓተ-ማህበር አዲስ አይደለም

የወጣቶች ማሕበራዊ ጉዳይ ተመራማሪዉ ቶማስ ጌንሲከ እንደሚለዉ በምስራቅ የሚታየዉ የቀኝ አክራሪ ህዝብ እንደ ምዕራቡ ሁሉ በቁጥር አነስተኛ ነዉ። የምስራቅ ጀርመን ወጣቶች ከምዕራቦቹ ይልቅ የፖለቲካ፥ የኢኮነሚ እና የማህበረሳባዊ ጉዳዮችን በማንሳት ከጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ ጋር ያነጻጽራሉ።ለዚህም ምክንያቱ አጥኚዉ እንደሚሉት የምዕራቡ ወላጅ፣ ትምሕርት ቤቶችና መገናኛ ዘዴዎች ከምሥራቁ በጣም በጎላ መንገድ በራስ የመተማመን ስሜትና ብዙዉን ነገር በግልፅ የማዉጣት ይትባሐልና መዋቅር ሥላላቸዉ ነዉ።

Matteo und Josephine auf dem Motorroller

ማቴዉና ዮስፊን በሞተር ብስክሌት

ጆሴፊን የመኖርያ ቦታዋን ቀይራ በምስራቅ ጀርመን በተለይም በትልልቅ ከተሞች መኖር እንደምትችል ትገልጻለች።በምዕራብ ጀርመን ከሚኖሩት ወጣቶች መካከል ወደ ምስራቅ ሄዶ ለመኖር ከሚችሉትና ከሚፈልጉት በጣም ጥቂት ወጣቶች አንዷ ናት ማለት ነዉ። አብዛኛዉ ወጣት ይህን አይፈልግም። ምክንያቱም ምዕራብ ጀርመን ለወጣቱ የወደፊት ተስፋ የሚሆን ብዙ ነገር ይገኛል ብለዉ ስለሚያምኑ ነዉ። በምስራቁ ክፍል የሚኖሩም ቢሆኑ በምዕራቡ ክፍል የተሻለ የትምህርት እና የስራ እድል እንደሚገኝ እና የፌደራል ጀርመን ስርአተ ማህበርም በትክክል ተግባራዊ ይሆናል የሚል እምነት አላቸዉ።

ቢርጊት ግሮትስ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ