ሃርትስ IV የጀርመን ሥራ ገበያ ና የማህበራዊ ድጎማ ለውጥ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 28.08.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ሃርትስ IV የጀርመን ሥራ ገበያ ና የማህበራዊ ድጎማ ለውጥ

በጀርመን የሥራ አጡን ቁጥር ለመቀነስና የማህበራዊ ድጎማ አሰጣጥን ለመለወጥ ሥራ ላይ የዋለው መርሃ ግብር 10 አመት አስቆጥሯል ። የመርሃ ግብሩ አዎንታዊና አሉታዊ ገፅታዎች እንዲሁም አርአያነቱ የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው

Hartz IV, Geld, Armut, Arbeitslosigkeit, Gesundheitsreform. de.fotolia.com/id/22040665

Hartz IV Symbolbild

በቀድሞው የጀርመን መራሄ መንግሥት ጌርሃርድ ሽሮደር ዘመነ መንግሥት በቮክስ ቫገን ኩባንያ ሃላፊ ፔተር ሃርትስ ተዘጋጅቶ የቀረበው የጀርመን ሥራ ገበያ ና የማህበራዊ ድጎማ ለውጥ 10 አመት ቢያስቆጥርም አሁንም አነጋጋሪ ነው  ። አጀንዳ 2010 ወይም ሃርትስ 4 በመባል የሚታወቀው ይኽው መርሃ ግብር ጀርመን አሁን ለደረሰችበት የእድገት ደረጃ ካበቋት ምክንያቶች አንዱ ተደርጎ ይወደሳል ። በሌላ በኩል መርሃ ግብሩ የሠራተኞችን መብት በመጫን በአንፃሩ ለአሰሪዎች ከልክ ያለፈ መብት በመስጠት ይተቻል ። ውዳሴናወቀሳየሚቀርብበትን ይህን አሰራር ከመነሻው ተግባራዊ ማድረግ ያስፈለገበት ምክንያት ምን ነበር ? እዚህ ጀርመን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በመምህርነት የሚያገለግሉት የምጣኔ ሃብት ምሁር ዶክተር ፈቃዱ በቀለ   

ያብራሩልናል ።

ILLUSTRATION - Spielzeugfiguren bauen am Schriftzug Hartz IV, aufgenommen am Dienstag (21.09.2010) in Schwerin. Die Bundesregierung steht in der Kritik wegen ihrer Pläne zur Hartz-IV-Reform. Die SPD warnt davor, eine Erhöhung der Regelsätze durch Kürzungen bei der Arbeitsmarktpolitik auszugleichen. Foto: Jens Büttner dpa/lmv (zu dpa 4033 vom 21.09.2010)

አዳዲስ የሥር መስኮችን ለመፍጠር አልሞ ሥራ ላይ በዋለው አጀንዳ 2010 የሥራ ና ሠራተኛ አገናኝ መሥሪያ ቤቶች በአዲስ መልክ እንዲዋቀሩ ተደረጓል ። ሌሎችም ለውጦች ተግባራዊ ሆነዋል ። በሃርትስ 4 ከተካሄዱት ለውጦች ዋነኛው የመንግሥት ወጪን ለመቀነስ የተወሰደው እርምጃ ነው ።

ሃርትስ 4 ተረቆ በቀረበበት እጎአ በ2002 በጀርመን የሥራ አጡ ቁጥር ከ4 ሚሊዮን በላይ ነበር ዛሬ ግን ይህ አሃዝ ወደ 2.8 ሚሊዮን ዝቅ ብሏል ። ለዚህም የሃርት 4 ድርሻ የጎላ መሆኑን አንዳንድ የመስኩ ባለሞያዎች ያስረዳሉ ። ዶክተር ፈቃዱ ግን ይህ የአጀንዳ 2010 ውጤት ብቻ ነው ሊባል አይችልም ይላሉ ።

ከሌሎችም ምጣኔ ሃብታዊ ምክንያቶች ጋር ተዳምሮ ጀርመን በአሁኑ ጊዜ ከሌሎቹ በኢንዱስትሪ ከበለፀጉ አገራት በተሻለ ደረጃ እንድትገኝ አብቅቷታል የተባለው አጀንዳ 2010 በተለያዩ አሉታዊ ገፅታዎቹም ይተቻል ።

Offene Hand mit 5 1 Euro-Stücken ILLUSTRATION - Ein-Euro-Stücke liegen am Sonntag (26.09.2010) auf der HAnd eines Mannes in Berlin. Die Erhöhung fällt minimal aus: Schwarz-Gelb will den Hartz-IV-Satz um bis zu 5 Euro im Monat anheben. Foto: Franz-Peter Tschauner dpa

ያም ሆኖ ጀርመን ከሌሎች የአውሮፓ ሃገራት ጋር በንፅፅር ሲታይ በተለይ ዝቅተኛ የወጣት ሥራ አጥ ቁጥር ያላት አገር ናት ። በኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ከሚገኙት አገራት ለምሳሌ ስፓኝ የወጣት ሥራ አጥ ቁጥር 50 በመቶ ሲደርስ በኢጣልያ ደግሞ 31 በመቶ ነው ። በፈረንሳይ  16 በመቶ ሲሆን በጀርመን ግን 8 በመቶ ብቻ ነው ። በጀርመን የወጣት ሥራ አጥ ቁጥር ሊያንስ የቻለበትን ምክንያትና ሌሎች አገራት ከጀርመን በአርአያነት ሊወስዱት የሚችሉትን አሰራር ዶክተር ፈቃዱ ይገልፃሉ ።

አጀንዳ 2010 ከድጋፉን ተቃውሞው ጋር ቀጥሏል ። ይህ እቅድ በሌላ መተካት አለበት የሚሉ ሃሳቦች አሉ ።

ዶክተር ፈቃዱ በማጠቃለያው እንዳሉት ደግሞ የጀርመንን የኢኮኖሚውን አቅጣጫ ከወዲሁ መተንበይ አይቻልም ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic