ሁለት አዲስ የፖለቲካ ድርጅቶች በትግራይ | ኢትዮጵያ | DW | 30.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ሁለት አዲስ የፖለቲካ ድርጅቶች በትግራይ

በትግራይ በተቃውሞ የፖለቲካ ረድፍ ለረዥም ግዜ ከሚታወቀው ዓረና ትግራይ ለላአላዊነትና ዴሞክራሲ በተጨማሪ ሌሎቾ ድርጅቶች ወደ ሰላማዊ ትግል ለመቀላቀል በሂደት ላይ መሆናቸው እየገለፁ ይገኛል፡፡ ሁለቱ አዳዲስ የፖለቲካ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሕጋዊ እውቅና ለማግኘት ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልፀዋል፡፡

በትግራይ በተቃውሞ የፖለቲካ ረድፍ ለረዥም ግዜ ከሚታወቀው ዓረና ትግራይ ለላአላዊነትና ዴሞክራሲ በተጨማሪ ሌሎቾ ድርጅቶች ወደ ሰላማዊ ትግል ለመቀላቀል በሂደት ላይ መሆናቸው እየገለፁ ይገኛል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ወደ ፓለቲካ ትግሉ የመቀላቀል ሂደት ላይ እንዳለ የገለፀው ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) የሚል ስያሜ የያዘ አዲስ የፖለቲካ ድርጅት በቀድሞ የዓረና አመራሮችና አባላት እንዲሁም ሌሎች የትግራይ ተወላጆች የተመሰረተ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ትግራይ የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት መሆንዋ የሚገልፀው የፖለቲካ ድርጅቱ ከዚህ በመነሳት ሁሉን አቀፍ ለውጥ የሚፈጥር የድርጅት ስትራቴጂ በመያዝ ለመንቀሳቀስ ወደ ፓለቲካ ትግሉ መግባቱ አብራርቷል፡፡


ከዚህ በተጨማሪ ባሳለፍነው ሳምንት ራሱን ያስተዋወቀው ሌላ የፖለቲካ ድርጅት ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የሚል ስያሜ አለው፡፡ ሶሻል ዲሞክራሲ ርእዮተ ዓለም ይዞ የሚንቀሳቀስ ብሄርተኛ ፓርቲ እንደሚሆን የገለፀው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ በትግራይ ጠንካራ መንግስት ለመመስረት እታገላለሁ ብሏል፡፡ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ባወጣው የመጀመርያው መግለጫ የትግራይ ህዝብ ለዘመናት አድርጎታል የሚለው ትግልና የተጎናፀፈው ድል ይጠቅሳል፡፡ በ1930ዎቹ አጋማሽ በትግራይ የነበረው 'ቀዳማይ ወያነ' በሚል የሚታወቀው አርሶአደሮች በአፄው ስርዓት ላይ ያደረጉት ተቃውሞ እንዲሁም ከ1960ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በትግራይ በህወሓት፣ ግገሓትና ሌሎች ያልተደራጁ እንቅስቃሴዎች ተጋድሎ ተቀጥያ መሆኑ ይገልፃል፡፡ ሳልሳይ ወያነ የፖለቲካ ድርጅት  በሂደት የተፈጠሩ የፖለቲካ ችግሮች በመጥቀስ ለፖለቲካዊ ችግር ፓለቲካዊ መፍትሔ የግድ ያስፈልጋል ይላል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት የሰጡን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የሕግና ስነ መንግስት ኮሌጅ መምህር ሸዊት ገብረእግዚአብሔር አዳዲሶቹ ፓርቲዎች ለትግራይ ህዝብ ተጨማሪ አማራጭ ይዘው ይመጣሉ ብለው እንደሚጠብቁ ለደቸ ቨሌ «DW» ተናግረዋል፡፡ ሁለቱ አዳዲስ የፖለቲካ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሕጋዊ እውቅና ለማግኘት ጥያቄ ማቅረባቸው ገልፀውልናል፡፡

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ


አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic