ሁለተኛ ዙር የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ  | ኢትዮጵያ | DW | 30.12.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ሁለተኛ ዙር የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ 

የአንበጣ መንጋው ሁለተኛ ዙር ወረርሽኝ በምስራቅ ሐራርጌ፣ ምስራቅ ባሌ እና ባሌ ዞኖች ከተከሰተ በኋላ በሄሊኮፕተር የታገዘ የኬሚካል ርጭት እየተደረገ መሆኑንም የኦሮሚያ ክልል ግብርና እና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ለዶይቼ ቬለ ገልጿል።የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ እንዳሉት አንበጣው ወደ ተጨማሪ ሶስት ዞኖች የመስፋፋት ስጋት አስከትሏል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:11

አሳሳቢው የአንበጣ መንጋ በኢትዮጵያ

የበረሃ አንበጣ መንጋ በኢትዮጵያ ዳግም በመስፋፋት በኦሮሚያ ክልል ሶስት ዞኖች በምርት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተነገረ። የአንበጣ መንጋው ሁለተኛ ዙር ወረርሽኝ በምስራቅ ሐራርጌ፣ ምስራቅ ባሌ እና ባሌ ዞኖች ከተከሰተ በኋላ በሄሊኮፕተር የታገዘ የኬሚካል ርጭት እየተደረገ መሆኑንም የኦሮሚያ ክልል ግብርና እና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ለዶይቼ ቬለ ገልጿል።የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ እንዳሉት አንበጣው ወደ ተጨማሪ ሶስት ዞኖች የመስፋፋት ስጋት ቢያስከትልም የሶማሊላነድ እና የኬንያ ድንበር አከባቢን ጨምሮ የመንጋውን ወረራ ለመቆጣጠር ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ ዘገባ አጠናቅሯል።

ስዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

Audios and videos on the topic