ሁለተኛው የሰብዓዊ መብት እና የዲሞክራሲ ጉባኤ | ዓለም | DW | 09.03.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ሁለተኛው የሰብዓዊ መብት እና የዲሞክራሲ ጉባኤ

የሰብዓዊ መብት የመቻቻል እና የዲሞክራሲ ዓብይ ጉባኤ ትናንት ጄኔቫ ውስጥ ተጀምሯል ። በዚሁ ጉባኤ ላይ ከ 67 አገራት የተውጣጡ በርካታ የየሀገራቸው አገዛዝ ስርዓት ሰለባዎች ፣ ጠንካራ ተችዎችና ዲፕሎማቶች ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር የተያያዙ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው ።

default

25 የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ቡድኖችን ባቀፈው ዓለም አቀፍ የሲቪል ማህበረሰብ ጥምረት የተዘጋጀው ይኽው ጉባኤ ከሚያተኩርባቸው ጉዳዮች አንዱ ከኢንተርኔት መረጃዎችን በነፃነት የማግኝት መብት መሆኑን ከአዘጋጆች አንዱ ዓለም ዓቀፍ የለዘብተኛ ወጣቶች ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ባርት ዎርድ ለዶይይቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል ። ያነጋገረቻቸው ሂሩት መለሰ ዝርዝሩን አዘጋጅታለች ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ