ሀና ግርማ እና አዲስ የሙዚቃ ስራዎቿ | ባህል | DW | 01.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ሀና ግርማ እና አዲስ የሙዚቃ ስራዎቿ

ሀና ግርማን ብዙዎች በኢትዮጵያ አይይል ውድድር ላይ ተመልክታችኋታል። በተለይ በልዩ የኦፔራ መዚቃ ተሰጥዎዋ ተደናቂነት ያተረፈችው አዳጊ ወጣት ሰሞኑን ሁለት ነጠላ ዘፈኖች አውጥታለች።

ሃና ሙዚቃውን እንዴት ተጫወተችው? የዚህን ሙዚቃ ዜማና ሙዚቃ ያቀናበረው እንዲሁም ሃናን የሚያሰለጥናት ቴድሮስ መኮንን( ቴዲ ማክ) መልስ ሰጥቶናል። እንዲሁም ሃና የኦፔራ ዘፈን እንድትዘፍን ያበረታታኝ ወንድሜ ነው ትላለች። ወንድሟ ታደሰ ግርማ ይባላል። በሙዚቃም ብቻ ሳይሆን በትምህርቷም እንድትበረታታ ይረዳታል።

ልጆች በልጅነት እድሜያቸው ታዋቂ ሲሆኑ አብዛኛውን ጊዜ የልጅነት ጊዜያቸውን በቅጡ አጣጥመው እንዳያድጉ የሚያደርገው የራሱ ሚና አለውና ከዚህስ አንፃር በቤተሰብ በኩል ምን አይነት ድጋፍ ሃና ታገኛለች? ሃና ብዙ አድናቂዎች አፍርታለች። ለነሱም መልዕክት አስተላልፋለች።

ስለሙዚቃ ስራዎቿ እና በህይወቷ ላይ ስለገጠማት ለውጥ ዛሬ በወጣቶች መድረክ የምንዳስሰው ይሆናል።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic