ሀብታሙን የጠቀመው ደሃ ተኮር የእድገት ፖሊሲ | ኢትዮጵያ | DW | 08.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ሀብታሙን የጠቀመው ደሃ ተኮር የእድገት ፖሊሲ

ኢትዮጵያ ላለፉት አስርት ዓመታት አስመዘገበች የተባለው የኤኮኖሚና የማኅበራዊ እድገት ደሀዉን ህብረተሰብ እንዳላቀፈ የተባበሩት መንግስታት የሰዉ ልጅ ልማት አመልካች ሠንጠረዥ ወይም «ሂውማን ዴቨሎፕመንት ኢንዴክስ» በጎርጎሮሳዊያኑ 2014 ባወጣዉ ርፖርቱ መዘገቡ ይታወሳል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:10

ደሃ ተኮር የእድገት ፖሊሲ

የማይክሮ ኤኮኖሚክስ እና የእድገት ፖሊሲ ምሁሩ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ፣ ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያት፣ መንግስት ደሃ ተኮር ብሎ የያዘዉ የእድገት ፖሊሲ ጥቂት ሀብታሞችን ብቻ እየጠቀመ ስለሆነ ነዉ ይለሉ። ደቡብ አፍሪቃ የሚገኘው« አዲስ የዓለም ሀብት» ወይም «ኒው ዎርልድ ዌልዝ» የተባለው የገበያ ጥናትና አማካሪ ድርጅት እንዳስታወቀዉ በኢትዮጵያ ወደ 2700 ሚሊየነሮች አሉ ። ይሁንና በአጠቃላይ ሲታይ በሃገሪቱ ኤኮኖሚያዊና ማህበረሰባዊ እድገቶች ውስጥ ከደሃዉ ይልቅ ጥቅት ባለፀጋዎች እየተጠቀሙ መሆኑን የ«ሂውማን ዴቨሎፕመንት ኢንዴክስ» ዘገባ ይጠቅሳል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኤኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል የኤኮኖሚክስ መምህር ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ በኢትዮጵያ በደሃና በሃብታም መሃል ያለዉ ልዩነት መጨመሩን ለዶቼ ቬሌ ሲያስረዱ፣ "አሁን እኛ የከተማ ዳታ ላይ ተመሰርተን የሰበሰብነዉ መረጃ የሚያሳየዉ በከተማ ዉስጥ በደሃና በሃብታም መሃል ያለዉ ልዩነት እየጨመረ ነዉ የሄደዉ። ገጠር ላይ ይህ ልዩነት ጥሩ አይታይም፣ ማለትም አልጨመረም፣ ግን ከተማ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮዋል። ስለዚህ እድገት ካለና የከተማዉ ደሃና ሃብታም ከጨመረ፣ የደሃዉ ችግር ደግሞ የ«ዩ ኤን ዲ ፒ» ጥናት እንደሚያሳየዉ ካልጨመረ፣ ያ ከዛ እድገት የሚገኘዉ ነገር ሌሎች ግሩፕ ዉስጥ ገብቶዋል ማለት ነዉ። እሄ ማለት ሁሉንም ያማከለ አይደለም ማለት ነዉ። ሁሉንም በእኩል ያዳረሰ አይደለም ማለት ነዉ።"


ለዚህ አይነት ችግር መፍትሄ ሊሆን የምችለዉ ይላሉ ፕሮፌሴሩ፣ «ዲስትሪቢውሽን ዊዝ ግሮውዝ» የሚሉት ነዉ መሆን ያለበት። እድገት ብቻዉ በቂ አይደለም። እድገት ለደህነት ቅነሳ አንደኛ መሰረታዊ ግብ ነዉ፣ ግን በቂ አይደለም ከእድገቱ አንፃር አንድ ላይ አብሮ የገቢ ስርጭትን አብረን ማየት አለብን። ስለዚህ የገቢ ስርጭቱ እንዴት ታስተካከለ የሚንለዉ የፖሊስ ጥያቄ ነዉ የሚሆነዉ። አንዱና ዋናዉ ደሆች የሚጠቀሙበት ሴክቴር ላይ ማተኮር አለብህ መጀመርያዉ ሲሆን፣ ሁለተኛዉ ግብር ገቢዎች ሃብታሙን ታክስ በማረግ ወደ ደሃዉ የሚፈስበት መንገድ መፍጠር አለብህ። ስለዚህ ከኤኮኖሚ ፖሊስ አንፃር የሚመረጠዉ የመጀመርያዉ ነዉ። መጀመርያዉኑ ደህነት ተኮር የሆነ ፖሊስ መንደፍና ደሆች የሚጠቀሙበት ስርዓት መዘርጋት አለብህ ማለት ነዉ። የኛ መንግስት እሄ ደህነት ተኮር ነዉ ፤ ነዉ የሚለዉ። ብያንስ የ«ዩ ኤን ዲ ፒ» ጥናት እንደምያሳየዉ ሁሉ አቀፍ አይደለም ነዉ፣ ስለዚህ የፖሊስ ችግር አለበት ማለት ነዉ።"

እንደ «ሂውማን ዴቨሎፕመንት ኢንዴክስ» ዘገባ ከሆነ ኢትዮጵያ በአማካይ ከ10 በመቶ በላይ ዓመታዊ የኤኮኖሚ እድገት እያሰመዘገበች ነው ፤ ለኤኮኖሚና ማህበራዊ መሰረተ ልማትም ብዙ መዋዕለ ንዋይም እያፈሰሰች ነው ። የደሃዉን ህብረተሰብ ኑሮን ለማሻሻልና ደህነትን ለመቀነስም ጥረት እየደረገች መሆኑን ዘገባው ይጠቀሳል። እነዚህ ጠቃሚ ዉጤቶች እንዳሉ ሆነው አሁንም ብዙሃኑ የሚገፋው የድህነት ህይወት ነው ። ይህም ሃገሪቱ በሰው ልጅ ልማት ረገድ አስጊ ሁኔታ ዉስጥ እንደምትገኝ የሚያሳይ መሆኑን ሰይጠቅስ አላለፈም። ምክንያቱም ይላል«ሂውማን ዴቨሎፕመንት ኢንዴክስ» ሪፖረቱ ወደ 25 ሚልዮን ኢትዮጵያውያኖች ከደህነት ወለል በታች የሆነ ህይወት ነዉ የሚመሩት። እነሱም ለችግር እና ለምግብ እጥረት ተጋለጭ ናቸው። ለዚህም ነዉ ይላል ዘገባዉ በጤና አገልግሎትና በትምህርት ጥራትም ሆነ በእርሻው ዘርፍ ከፍተኛ ችግር የምታየዉ።

እርሻዉ ላይ እንደታቀደዉ ያህል ቢሠራ የምግብ እጥረቱን የመቀነስ ሚና እንዳለዉ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። "የኢትዮጵያ እርሻ አንደኛ መሠረታዊ ችግሩ ዝናብ ላይ ጥገኛ መሆኑ ነዉ። አሁን ባለፉት 24 ዓመታት ከዝናብ ጥገኝነት የመዉጣት ሥራ አልተሰራም። በእኔ ግምት ለምን ብትል አጠቃላይ በመስኖ መልማት የሚችል መሬት አንድ በመቶ እንኳን አይሞላም። ነጥብ ሰባት በመቶ ብቻ ነዉ መስኖ የሆነዉ። ስለዚህ አንድ ነጥብ በማይሞላ የመስኖ ሥራ ዘላቂ የሆነ የእርሻ ምርት ወይም የምግብ ምርት ሊኖር አይችልም።"


በኤኮኖሚ እድገት የአፍሪቃ ነብር ተብለ የምትጠራው ኢትዮጵያ ከፍተኛ ድርቅ ባስከተለዉ ችግር ወደ 15 ሚልዮን ህዝቦቿ ከፍተኛ የምግብ ርዳታ እንደምያስፈልጋቸዉ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ርዳታዎች አስተባባሪ በምህፃሩ «ኦቻ» ማስጠናቀቁ ይታወሳል።

መርጋ ዮናስ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic