«ሀሳቡን ያገኘሁት ከዱባይ ነው» | ባህል | DW | 05.12.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

«ሀሳቡን ያገኘሁት ከዱባይ ነው»

በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ «አዲስ ሾፒንግ ፌስቲቫል» የተባለ ፌስቲቫል አዲስ አበባ ውስጥ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ስለ ፌስቲቫሉ ምንነት እና ይዘት በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት እንቃኛለን።

በአዲስ አበባ ከተማ ከህዳር 8 ቀን አንስቶ ለ 21 ቀናት የሚቆይ ፌስቲቫል በመካሄድ ላይ ይገኛል። ይሔ ፌስቲቫል «አዲስ ሾፒንግ ፌስቲቫል» ይባላል። አዘጋጁ ደግሞ ሚካኤል ፋሲል ነው። የሚካኤል ስራ እና እቅድ ብዙም ኢትዮጵያ ውስጥ የተለመደ አይደለም ። በዚህም የተነሳ ሚካኤል ስለ ፌስቲቫሉ ለማያውቁ ጎብኚዎች ወይም ታዳሚዎች ብዙ ማብራራት ይጠበቅበታል።

በ28 ዓመቱ ሚካኤል ተነሳሽነት የተዘጋጀው የ«አዲስ ሾፒንግ ፌስቲቫል» በዓይነቱ የመጀመሪያው ይሁን እንጂ፤ በተለይ እንደ ዱባይ ባሉ ከተሞች በከፍተኛ መጠን ይካሄዳል። ዱባይ ይህንኑ ፌስቲቫል ስታካሂድ ዘንድሮ 20ኛ ዓመት ሊሞላት ነው። ከተማዋም ከአንድ ወር በኋላ የሚካሄደውን ፌስቲቫል በማስተዋወቅ ላይ ትገኛለች።ከሶስት ባልደረቦቹ ጋር በመሆን ሃሳቡን ለአዲስ አበባ ተስማሚ አድርጎ ለማዘጋጀት የተነሳው ሚካኤልም የዓላማው መነሻ ዱባይ ናት።

የ« ዱባይ ሾፒንግ ፌስቲቫል» ለመጀመሪያ ጊዜ በዱባይ ከተማ እኢአ በ 1996 ዓም ሲካሄድ፤ በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን የሀገሪቱ መንግሥት ነው ያዘጋጀው። የ« ዱባይ ሾፒንግ ፌስቲቫል» እጅግ ዝነኛ እየሆነ በመምጣቱም ዝግጅቱ በሚካሄድባት የጥር ወር ከተማዋ በመብራት ታሸበርቃለች፤ ጎብኚዎችን ለመሳብ በንግድ እቃዎች ላይ ነጋዴዎች ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ እና ማስታወቂያ ያደርጋሉ፣ ለህፃናት እና ለቤተሰብ ልዩ የመዝናኛ ዝግጅቶች በከተማዋ ይሰናዳሉ። ሌላም ሌላም ። ወደ ኢትዮጵያ የተመለስን እንደሁ የመጀመሪያው የ« አዲስ ሾፒንግ ፌስቲቫል» ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ነው የቀሩት፤ ሚካኤል ጅማሬውን እንዴት ይገመግመዋል? በዚህ ፌስቲቫል ከተካፈሉም የንግድ ባለቤቶች አንዱን አነጋግረናል። ሙሉውን ዝግጅት በድምፅ ከዚህ በታች ያገኙታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic