የሲዳማ አስተዳደር የሲአን መስራች አስተያየት
ሐሙስ፣ ሐምሌ 11 2011ማስታወቂያ
የሲዳማ ዞን የወደፊት እስተዳደርን ለመወሰን የሚሰጠዉ ድምፅ (ሕዝበ ዉሳኔ) በሲዳማ ዞን የሚኖሩ የሁሉም ብሔረሰብ ተወላጆች የሚሳተፉበት እንጂ የሲዳማ ሕዝብ ብቻዉን የሚወስንበት እንደማይሆን ከሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) መስራቾች አንዱ አስታወቁ። በ1970 ሲአንን ከአባታቸዉ ከአቶ ወልደአማኑኤል ዱባለ ጋር ሆነዉ የመሰረቱት አቶ ደጀኔ ወልደአማኑኤል እንደሚሉት በአስተዳደሩ ጉዳይ በሲዳሞ ዞን በሚገኙ አካባቢዎች የሚኖረዉ የየትኛዉም ብሔር ተወላጅ ሐሳቡን በነፃነት የመስጠትና የመወሰን መብቱ ሊከበርለት ይገባል። የሲዳማ ሕዝብ የወደፊት አስተዳደሩን ለመወሰን ሕዝበ ዉሳኔ መደረግ የነበረበት እስከ ዛሬ ነበር ብለዉ የሚያምኑ የሲዳማ ተወላጆች ግን ዛሬ ከፀጥታ አስከባሪዎችና ከሌሎች ብሔር ተወላጆች ጋር እየተጋጩ ነዉ። ስዊትዘርላንድ የሚኖሩት አቶ ደጀኔ እንደሚሉት ግን ሰዎች ከሌላ አካባቢ መጥተዋልና «አያገባችሁም» ሊባሉ አይገባም። አቶ ደጀኔን ነጋሽ መሐመድ በስልክ አነጋግሯቸዋል።
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ