1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቃለ ምልልስ ከተመስገን ደሳለኝ እና ወይንሸት ሞላ ጋር

ዓርብ፣ መጋቢት 28 2010

ዶቼቬለ ያነጋገራቸው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ፖለቲከኛ ወይንሸት ሞላ እስር ቤት ውስጥ እጅግ ጠባብ በሆኑ ክፍሎች ከሌሎች በርካታ እስረኞች ጋር ተፋፍገው መቆየታቸውን ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/2vdHw
Journalist Temesgen Desalegn
ምስል DW/Y. Geberegziabeher

ቃለ ምልልስ ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጋር

መጋቢት 16 2010 ዓም፣ ከሳምንታት በፊት ከእስር ለተፈቱ፣ በተዘጋጀ የምሥጋና መርሐ-ግብር ማብቂያ ላይ ታስረው ትንናት ከእስር የተለቀቁት ጋዜጠኞች ፖለቲከኞች እና ጦማሪዎች የእስር ቤት አያያዛቸው እጅግ አሰቃቂ እንደነበረ ተናገሩ። ዛሬ ዶቼቬለ ያነጋገራቸው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ፖለቲከኛ ወይንሸት ሞላ፤ እነርሱ እና ሌሎች እስረኞች እጅግ ጠባብ በሆኑ ክፍሎች ከሌሎች በርካታ እስረኞች ጋር ተፋፍገው መቆየታቸውን ተናግረዋል። ትናንት ከተፈቱት ከ11ዱ አብዛኛዎቹ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ የታሰሩ ናቸው። የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት አባል ወይዘሪት ወይንሸት ሞላ በተደጋጋሚ ይታሰሩ ከነበሩት መካከል አንዷ ናት። ፖለቲከኛ ወይንሸት ሞላ እና ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ስለ ዐሥራ ሁለቱ ቀናት የእስር ቆይታቸው ጠይቀናቸዋል።  

ከሁለቱም ጋር የተደረጉት ሙሉ ቃለ መጠይቆቹ ከታች የድምፅ ማዕቀፎቹ ውስጥ ይገኛሉ። 

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ