1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፖለቲካዊ ነውጥ በበርሊን

ዓርብ፣ ኅዳር 18 2002

ከሶሶት ወር በፊት በአፍጋኒስታን ስላተካሄደው የዓየር ድብደባ ትናንት በድብቅ ከቀረበው ዘገባ በኃላ የጀርመን መንግስት ጉዳዩ በቀጥታ በሚመለከታቸው ባለስልጣናት ላይ ዕርምጃዎችን ወስዷል

https://p.dw.com/p/Kj8l
ከስልጣን የወረዱት ዮንግ እና ጀነራል ሽናይደርሀንምስል AP

ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸው የጀርመን ወታደራዊ ባለስልጣንና የዚያን ጊዜው የጀርመን መከለከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ ከስልጣን ተነስተዋል ። የየኔው መከለከያ ሚኒስትር ፍራንስ ዮሴፍ ዩንግም ዛሬ ከስራቸው ተሰናብተዋል ። አዲሱ የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር Karl Theodor zu Guttenburg መረጃው ከህዝቡም ሆነ ከአቃቤ ህግ ተደብቆ መቆየቱን አረጋግጠዋል ። አሁን ዋናው ጉዳይ የጀርመን መከለካያ ሚኒስቴር በጥቃቱ ሰላማዊ ሰዎች ስለመገደላቸው መቼ ነበር ማወቅ የቻለው የሚለው ነው ።

ቤርንት ራይገርት ፣ ሂሩት መለሰ