1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፒዮንያንግ፤ የኪም ዮን ልጅ ለስልጣን መብቃት

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 19 2004

ሰሜን ኮርያ ፈላጭ ቆራጭ ይሰኙ የነበሩትን መሪዋን ሸኝታ ልጃቸዉን ስልጣን ላይ አወጣች።

https://p.dw.com/p/13baL
ኪም ዮንግ ዑንምስል AP

በዛሬዉ ዕለትም በመቶዎችና ሺዎች የተገመተ ህዝብ በፒዮንግያንግ አደባባይ ለሟቹ ፕሬዝደንት መታሰቢያ መዉጣቱ ተዘግቧል። ለአባታቸዉ ሃዘን አደባባይ የወጣዉን ህዝብ ሲመለከቱ የዋሉት የፕሬዝደንት ኪም ዮንግ ኢል ሶስተኛ ልጅ ኪም ዮንግ ዑን የአገሪቱ የበላይ መሪ ተብለዉ ዛሬ ተሰይመዋል። ዮንግ ዑን በአባታቸዉ እግር ለመተካት ወታደራዊና መንግስታዊ ባለስልጣናትን ጨምሮ ጠንከር ያለ የህዝብ ድጋፍ እንዳገኙ ቢነገርም የተለየ ነገር በአስተዳደር ረገድ እንደማይጠበቅ ነዉ ደቡብ ኮርያ ሴዑል የሚገኘዉ የፍሬደሪሽ ናዉማን ተቋም ኃላፊ ቫልተር ክሊትስ የጠቆሙት፤
«በመጀመሪያ ምንም ለዉጥ አልጠብቅም። ምክንያቱም ኪም ዮንግ ዑንን ለስልጣን ያመቻቿቸዉ ሰዎች የኪም ዮንግ ኢል እና የኪም ኢል ሱንግ ትዉልዶች ናቸዉ። አንዳንዶቹ 70 ሌሎቹም በ80ዎቹ ዓመታት መጀመሪያ የእድሜ ክልል ይገኛሉ። ወጣት የሚባሉ ዩንግ ሱንግ ቴክ 68ዓመታቸዉ ነዉ። እናም እነዚህ ሰዎች በሚሳተፉበት ሁኔታ በፖለቲካዉም ሆነ በኤኮኖሚዉ ለዉጥ አልጠብቅም።»

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ