1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ፍላጎቴ ሰርቶ መለወጥ ነው» -ወጣት ሰላም

ዓርብ፣ ነሐሴ 10 2005

ሰላም በንግዱ ዘርፍ የተሰማራች እና የራሷ ሱቅ ያላት የ 19 ዓመት ወጣት ናት። ንግዷን በሙሉ ኋላፊነት እንዴት እንደምትወጣው ገልፃልናለች።

https://p.dw.com/p/19QZB
ምስል DW/A. Ilin

ሰላም ጠንክር የደብረዘይት ወይንም ቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪ ናት። ከሁለት ዓመት ጀምሮ በንግዱ ዓለም የተሰማራችው ሰላም፤ በወንድሟ ድጋፍ የሚመጡላትን አልባሳት እና ጫማዎች ትሸጣለች። በዚህም ስኬታማ መሆኗን ትናገራለች።

ሰላም ትምህርቷን እስከ 10ኛ ክፍል ነው የተከታተለችው። «ቀጥሎ ለመማር ውጤት አልመጣልኝም » ትላለች።

ሰላም ወደ ንግድ ከመግቧቷ በፊት ሌላ ስራም ሞክራለች። በሙያው ብዙም አትግፋበት እንጂ የፀጉር ስራ ወይንም የፀጉር ፋሽን ስልጠና ወስዳለች።

ለሰላም ቤተሰብም ይሁን ለርሷ ንግድ አዲስ ነገር ስላልነበር በመጨረሻም ለንግድ ስራ ወሰነች። ለዚህ ስራዋም ብዙ ገንዘብ መበደር ነበረባት። ትርፋማ ባልሆንስ የሚል ስጋት ግን አልነበራትም።

ከ 16 ዓመቷ ጀምሮ በቋሚነት የስራውን ዓለም የተቀላቀለችው ሰላም ያላትን ልምድ አካፍላናለች። ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሒሩት መለሰ