1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፈረንሳይ ለፍፃሜው ደረሰች

ረቡዕ፣ ሐምሌ 4 2010

ሩሲያ ላይ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ትናንት ምሽት በተደረገው እና ሁለቱን ጎረቤት ሃገራት ቤልጅየም እና ፈረንሳይን ባገናኘው ጨዋታ ፈረንሳይ ድል ቀንቷታል። ፈረንሳይን ለፍፃሜው ጨዋታ ያደረሳትን ግብ ተከላካዩ ሳሙኤል ዩን ኪቲ በጭንቅላቱ ገጭቶ ያስቆጠረው ብቸኛ ጎል ነው።

https://p.dw.com/p/31HrW
Fussball Kroatische Mannschaft WM 1998 - Zvonimir Boban
ምስል picture-alliance/dpa/M. Gallardo

ከፍፃሜ ለመድረስ 12 ዓመታት ወስዶባታል

ፈረንሳይ በዓለም ዋንጫ ለመጨረሻ ጊዜ ለፍፃሜው ጨዋታ የቀረበችው በጎርጎሪዮሳዊው የዘመን ቀመር 2006ዓ,ም ጀርመን ላይ በተካሄደው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ ጊዜ ነበር። ቡድኑ ለዚህ በመድረሱ ብቻ ሳይሆን በተጫዋዎቹ ብቃትም የተደሰቱት ፈረንሳውያን ትናንት ምሽቱን የፓሪስን ዋና ዋና ጎዳናዎች በሰንደቅ ዓላማቸው እና በርችቶች ታጅበው ደስታቸውን ገልጸዋል። ይህ የድል ስሜትም በመላው የፈረንሳይ ከተሞች መስተጋባቱን ፓሪስ የምትገኘው ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ በላከችው ዘገባ ጠቅሳለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ