1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፈረንሳይን ያስቆጣዉ የብሪታንያ የአዉስትራልያና የአሜሪካ ስምምነት

ማክሰኞ፣ መስከረም 11 2014

ከፕሬዝዳንት ባይደን  ወደ ስልጣን መምጣት ጋር ይሻሻላል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የአውሮጳ ህብረትና አሜሪካ ግንኙነት፤ አሁን ላይ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳልሆነ ነው የሚታየውና የሚሰማው። ፈረንሳይ የብሪታንያ የአዉስትራልያና የአሜሪካ ማለትም የሦስትዮሹ ወታደራዊ ግንኙነት ቀጥተኛ ተጠቂ ናትም እየተባለ ነው።

https://p.dw.com/p/40cJl
EU und US Fahne
ምስል Imago/Manngold

ስምምነቱ የህብረቱንና አሜርካንን ግንኙነት የበለጠ እንዳሻያክረው አስግቷል

ከፕሬዝዳንት ባይደን  ወደ ስልጣን መምጣት ጋር ይሻሻላል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የአውሮጳ ህብረትና አሜሪካ ግንኙነት፤ አሁን ላይ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳልሆነ ነው የሚታየውና የሚሰማው። ፕሬዝዳንት ባይደን በተለይ ከአውሮጳ ህብረት ጋር ወዳጅነታቸውን እንደሚያጠናክሩ ሲገልጹ የነበር ቢሆንም፤ በቅርቡ በአፍጋኒስታን ጉዳይ በተናጠል የወሰዱት እርምጃና ባለፈው ሳምንት ደግሞ ከብሪታኒያና አውስትራሊያ ጋር የፈረሙት የሦስትዮሽ ወታደራዊ ስምምነት ግን ይልቁንም የህብረቱን እና አሜርካንን ግንኙነት የበለጠ እንዳሻያክረው አስግቷል። ፈረንሳይ የሦስትዮሹ ወታደራዊ ግንኙነት ቀጥተኛ ተጠቂ ናትም እየተባለ ነው።

አዜብ ታደሰ 

ገበያዉ ንጉሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ