1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጣናን ለመታደግ ከካናዳ ማሽን ሊላክ ነው

ዓርብ፣ የካቲት 16 2010

በአደገኛነቱ የሚታወቀውን እሞቦጭን ከጣና ሐይቅ ላይ ለማስወገድ የሚደረገው ጥረት አልተቋረጠም። እምቦጭ ከዓለማችን አሥር አደገኛ አረሞች አንዱ ነው።  ዐረሙን በሰው እጅ ለማስወገድ የተደረገው ከፍተኛ ርብርብ የሚፈለገውን ያኽል ውጤት እንዳላስገኘ ይነገራል።  የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዐረሙን ከሐይቁ ላይ የሚያጭድ ማሽን አምርቶ ሙከራ እያደረገ ይገኛል።

https://p.dw.com/p/2tEez
Äthiopien Kampagne Save Lake Tana
ምስል Kalkidan Tsena

እምቦጭን ከጣና የሚያጭድ ማሽን ከካናዳ

በአደገኛነቱ የሚታወቀውን እሞቦጭን ከጣና ሐይቅ ላይ ለማስወገድ የሚደረገው ጥረት አኹንም አልተቋረጠም። እምቦጭ ከዓለማችን አሥር አደገኛ አረሞች አንዱ ነው።  ዐረሙን በሰው እጅ ለማስወገድ የተደረገው ከፍተኛ ርብርብ የሚፈለገውን ያኽል ውጤት እንዳላስገኘ ይነገራል።  የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዐረሙን ከሐይቁ ላይ የሚያጭድ ማሽን አምርቶ ሙከራ እያደረገ ይገኛል። ካናዳ ውስጥ ነዋሪ የኾኑ ተቆርቋሪዎችን የሚያስተባብረው ኢትዮ ካናዳውያን ግብረ-ኃይል በበኩሉ ዐረሙን ከሐይቁ ላይ የሚያስወግድ ማሽን ገዝቶ ለመላክ ገንዘብ ለማሰባሰብ በዝግጅት ላይ እንዳለ ተገልጧል። ነዋሪዎቹ ገዝተው ወደ ኢትዮጵያ ሊልኳቸው ያሰቡት ሁለት አይነት ማሽኖችን ነው። አንደኛው ማሽን መካከለኛ የፈረስ ጉልበት ያለው ሲሆን፤ መጓጓዛውን ሳይጨምር ዋጋው 49,980 የአሜሪካ ዶላር እንደሆነ ተገልጧል። ሁለተኛው ማሽን ከፍተኛ የፈረስ ጉልበት ያለው ሲሆን 150,000 ዶላር ግድም ያወጣል ተብሏል። የቶሮንቶው ዘጋቢያችን አክመል ነጋሽ ዝርዝሩን ልኮልናል።

አክመል ነጋሽ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ