1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

“ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ይልቀቁ” የኦሮሞ ተቃውሞ አራማጆች

ዓርብ፣ ሰኔ 26 2012

የኦሮሞ ተቃውሞ አራማጆች የድምፃዊ ሐጫሉ ሑንዴሳ ግድያ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ፣ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአፋጣኝ ሥልጣን እንዲለቁ እንዲሁም የታሰሩ ፖለቲከኞች እንዲፈቱ ግፊት እያደረጉ ነው። በማኅበራዊ ድረ ገፆች የቀረቡት ሰባት ጥያቄዎች ናቸው። መልስ ካልተሰጠ በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ይሻሉ

https://p.dw.com/p/3ekjJ
Äthiopien | Nobelpreis | Premierminister Abiy Ahmed Ali
ምስል Getty Images/AFP/F. Varfjell

በማኅበራዊ ድረ ገፆች በሚካሔደው ዘመቻ ሰባት ጥያቄዎች ቀርበዋል

ድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ተገድሎ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ 35 ሰዎች ከታሰሩ በኋላ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የተቃውሞ ዘመቻ በመካሔድ ላይ ይገኛል። ፌስቡክ እና ትዊተርን በመሳሰሉ ማኅበራዊ ድረ ገፆች በሚካሔደው ዘመቻ ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል የድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ፣ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአፋጣኝ ሥልጣን እንዲለቁ፣ የዘፈቀደ ግድያዎች ይቁሙ የሚሉት ይገኙበታል። 

ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፤ በሚቀጥሉት አምስት ወራት ነጻ እና ፍትኃዊ ምርጫ እንዲካሔድ፤ የተቋረጠ የኢንተርኔት እና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት ወደ ሥራ እንዲመለስ የሚሉ ጥያቄዎችም ቀርበዋል። 

እነዚህ ጉዳዮች መልስ ካልተሰጣቸው በጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ላይ ዓለም አቀፍ ማዕቀብ እንዲጣልም ግፊት ያደርጋል። እሸቴ በቀለ ተቃውሞውን የሚያስተባብሩትን ዶክተር ሔኖክ ገቢሳን በስልክ አነጋግሯቸዋል።

እሸቴ በቀለ

ኂሩት መለሰ