1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠቅላይ ሚንሥትሩ ከተለያዩ ፓርቲ መሪዎች ጋር ተወያዩ

ቅዳሜ፣ ጥር 25 2011

ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጋር ዛሬ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪቃ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ECA) አዳራሽ ውይይት አካሄዱ። በውይይቱ ጠቅላይ ሚንሥትሩን ጨምሮ «ከ4 የፖለቲካ ድርጅት» መሪዎች የውይይት ጽሑፍ ቀርቧል።

https://p.dw.com/p/3CchF
Äthiopien Diskussion zwischen den PM Abiy Ahmed und Opposition
ምስል DW/Y.-G. Egiziabher

የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ ውይይት

ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጋር ዛሬ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪቃ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ECA) አዳራሽ ውይይት አካሄዱ። በውይይቱ ጠቅላይ ሚንሥትሩን ጨምሮ «ከ4 የፖለቲካ ድርጅት» መሪዎች የውይይት ጽሑፍ ቀርቧል። ከዛሬው ውይይት አስተባባሪ አንዱ የኾኑት የሺዋስ አሰፋ፦«የመድረኩ ዋና አላማ በዚህ የፖለቲካ ሽግግር ወቅት የፖለቲካ አመለካከትን በሰላማዊ ሁኔታ የመለዋወጥ ልምድን ለማሰደግ ነው» ብለዋል። በውይይቱ፦  «ስለ ዲሞክራሲያዊ የፖለቲካ ባህልና ብዝኃነት» የሚል ጥናታዊ ጽሑፍ በጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ ቀርቧል። የሕወሓት አመራር በነበሩበት ጊዜ ላጠፉት ጥፋት በመድረኩ ኹለት ጊዜ ይቅርታ የጠየቁት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ «የብሔር ብሔረሰቦች ጥያቄ» የሚል ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ «የፖለቲካ ፓርቲዎች ምስረታ ጥያቄ፤ የሲቪክ ማኅበራትና ሚዲያ ሚና በዲሞክራሲ ግንባታ» በሚል፤ ዶ/ር መረራ ጉዲና ደግሞ «ፌዴራሊዝም በኢትዮጵያ» በሚል ርእስ ጥናት አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ውይይት፦ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አራት እና አምስት ሰብሰብ ቢሉ የተሻለ ውጤት እንደሚያስመዘግቡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሳስበዋል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ