1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግጭት አፈታትና የሰላም ጉባኤ

ዓርብ፣ መጋቢት 3 2002

ለአርብቶአደሩ ዋነኛዉ ነገር ለመወያየት የለያዩ ወገኖችን በጋራ መገናኘት መቻላቸዉ ነዉ። ለዚህ ነዉ እኛ የምንደግፋቸዉ፤ ተገናኝተዉ እርስ በርስ እንዲወያዩ ለማድረግ

https://p.dw.com/p/MRbT
ምስል dpa - Fotoreport

ግጭት አፈታትና የሰላም ጉባኤ

በተለያዩ አገራት የሚነሱ ግጭቶችን ለማስወገድ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የየበኩላቸዉን ሚና እጫወታሉ። በጀርመን የሲቪል ማኅበረሰብ ትብብር የሚንቀሳቀሰዉና የሰላም አማካሪዎችን በተለያዩ አገራት በመላክ የግጭት አፈታት የልምድ ልዉዉጥ የሚያደርገዉ ፕሮጀክት በአፍሪቃም የበኩሉን በማድረግ ላይ ነዉ። ሰሞኑን በኢትዮጵያም ተመሳሳይ ልምድ ለመለዋወጥ ያስቻለ ጉባኤ ተካሂዷል፤ የፕሮጀክቱን አስተባባሪና ከተሳታፊዎች መካከልም በማነጋገር ሸዋዬ ለገሰ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

የሲቪል ሰላም አገልግሎት በእንግሊዝኛ ምህፃሩ CPS የተሰኘዉ ፕሮጀክት የጀርመን ሲቪል ማኅበረሰብ ትብብር የሚንቀሳቀስ የጀርመን የልማት አገልግሎት ድርጅት ነዉ። ይህ ድርጅት በተለያዩ አገራት የግጭት መንስኤዎችን በማጥናት ሰላምን በማኅበረሰቡ ዉስጥ ለማስፍን በመስራት ላይ ይገኛል። በአፍሪቃ በላቲን አሜሪካና በእስያ በበርካታ አገራት አጋር ድርጅቶቹ አማካኝነት ተግባሩን ያከናዉናል። በየጊዜዉም በየክፍለ ዓለማቱ በሚንቀሳቀሱት የሰላም አማካሪዎች አማካኝነት የግጭት አፈታት ልምዶችን ይለዋወጣል። በአፍሪቃ በየሶስት ዓመቱ የሚካሄደዉ ተመሳሳይ የልምድ መለዋወጫ መድረክ ዘንድሮ በኢትዮጵያ ለአምስት ቀናት ተካሂዷል። በኢትዮጵያ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ክላዉዲያ ሆይፈር ስለጉባኤዉ ዓላማ ሲገልፁ፤

«ዋናዉ ዓላማዉ የሲቪል ሰላም አገልግሎት አባል አገራት ልምድ እንዲለዋወጡ ማድረግ ነዉ። ልምድ ልዉዉጡ አንድ ነገር ሆኖ የሲቪል ሰላም አገልግሎት ተግባራትን ለማፋጠን፤ እንዲሁም ሰላምን ለመገንባት ግጭቶች የሚፈቱባቸዉን መንገዶች ማመቻቸትንም ይመለከታል።»

ባለፈዉ ሳምንት በአርባምንጭ ከተማ በተካሄደዉ የሰላም ጉባኤ የኬንያ፤ ኒዠር፤ ሩዋንዳ፤ ቡሩንዲ፤ ሱዳን፤ እንዲሁም ዚምባቡዌ፤ ዑጋንዳና ኢትዮጵያ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። እንዲያም ሆኖ በተጠቀሱት አገራት የሚታዩት ግጭቶች ይለያያሉ። እንደፕሮጀክት አስተባባሪዋ ገለፃ ለምሳሌ በኢትዮጵያ፤ ዑጋንዳና ኒዠር በአርብቶ አደሩ ማኅበረሰብ መካከል የሚከሰቱ ግጭቶች ዋነኛ ናቸዉ።

ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ ተግባሩን ከጀመረ ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ከመንግስታና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋ በተመተባበር ሲሰራ የሚያተኩርባቸዉ ሁለት የግጭት ዓይነቶች አሉ፤

«በኢትዮጵያ በሁለት የግጭት አካባቢዎች እናተኩራለን። አንዱ የአርብቶአደሮች ግጭት ሲሆን ሌላኛዉ የድንበር ግጭት ነዉ፤ በኦሮሚያና በደቡብ ብሄር ብሄረሰብ ክልል። በየጊዜዉ ልምድ እንለዋወጣለን፤ የስልጠና ዘርፍም አለን፤ በባህሎች መካከል ግንኙነቶችን መፍጠር፤ የሰላም ተመክሮዎችንም መጋራት የመሳሰሉ ተግባራትን በኢትዮጵያ ካለን ቀጥተኛ ተግባር ጋ በማገናኘት እንሰራለን።»

ፕሮጀክቱ ተግባሩን ከመጀመሩ አስቀድሞ ጥናት ያካሄደ መሆኑን አስተባባሪዋ ገልጸዉ በአርብቶ አደሮች መካከል ለሚፈጠሩ ግጭቶች ማስወገጃ ያሏቸዉን ስልት ያብራራሉ፣

«ለአርብቶአደሩ ዋነኛዉ ነገር ለመወያየት የለያዩ ወገኖችን በጋራ መገናኘት መቻላቸዉ ነዉ። ለዚህ ነዉ እኛ የምንደግፋቸዉ፤ ተገናኝተዉ እርስ በርስ እንዲወያዩ ለማድረግ። በዚህም ለችግሮቻቸዉ መፍትሄ ለማምጣት እንዲችሉ ያግዛል።»

የአርባምንጩን ጉባኤ ተከትሎ በብሄራዊ ደረጃ በአጋርነት የሚሰሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሰላም አማካሪዎችን ያሰባሰበ የመማማሪያ መድረክ ጅንካ ላይ ተካሂዷል። የዚህ መድረክ ተካፋይ የሆኑት የአዋሳ የሲቪል ማኅበረሰብ መረጃ ማኅከል ማኅበር የተሰኘዉ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ዳይሬክተር አቶ ኩስያ በቀለ በደቡቡ የአገሪቱ ክፍል የሚንቀሳቀሰዉ ድርጅታቸዉ በየጊዜዉ በአካባቢዉ የሚነሱ ግጭቶችን ለማስቀረት ስለሚያደርገዉ እንቅስቃሴ ሲገልፁ፤

ሸዋዬ ለገስ

ነጋሽ መሐመድ