1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግብፅ የጋዛ ድንበሯን በከፊል ከፈተች

ማክሰኞ፣ ግንቦት 23 2003

ለአራት አመታት ከተዘጋ በኋላ ግብፅ ለጋዛ ነዋሪዎች ቅዳሜ ዕለት ድንበሯን ከፈተች። ህጉ ለጊዜው የተፈቀደው ለሴቶች፤ ለህፃናትና ከ40 ዓመት በላይ ለሆኑ ወንዶች ነው።

https://p.dw.com/p/RQt9
የፍልስጤም ነዋሪዎች ድንበር ሲሻገሩምስል AP

የመጀመሪያው አውቶባስ ተሳፋሪዎችን ይዞ የፊልስጤምን ክልል አልፎ ድንበር ላይ የምትገኘውን የ ራፋህ ከተማ ተሻግሯል። 400 የሚሆኑ ሰዎችም ድንበር የሚያሻግረውን ጉዞዋቸውን እየጠበቁ ነው። ይህም ለብዙ ፍልስጤሚያውያን ዕረፍት ሰጥቷል። በሌላ በኩል ደግሞ እስራኤልን ሀሳብ ላይ ጥሏታል። እንደውም የዚህ ድንበር መከፈት፤ በቀላሉ በህግ ወጥ መንገድ የጦር መሳሪያዎች አስርጎ ለማስገባት መንገድ ይከፍታል ይላሉ፤ ግሀሺ ሐማድ፤ የሀማስ መንግስት የውጭ ጉዳይ ተወካይ።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ