1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጋዜጠኛዉ

እሑድ፣ ሐምሌ 14 2011

ከቀኑ አምስት ግድም።አንዲት ሞተር ብስክሊት ዉልብ አለች።መኪና ተከተላት።መኪናዋን ሌላ መኪና።ሌላዋን መኪና ሌላ ሞተር ብስክሌት።ጋዜጠኛዉ አንጋጥሶ ሲመለከት ከሁለቱ መኪኖች አንደኛዋ ዉስጥ ሰዉዬዉን አያቸዉ

https://p.dw.com/p/3MJqF
Tsegaye Tadesse Journalist  Äthiopien
ምስል privat

የጋዘጠኛ ፀጋዬ ታደሰ ገጠመኝ

ግንቦት 12 1983።መሽቷል።እሱ ግን አልተኛም።ስልኩ አቃጨለ።ደገመ።የጋዜጠኛ ሥልክ እረፍት የለዉም።ብዙም ሳይቻኮል አነሳዉ።ከወዲያኛዉ ጫፍ ያለዉ ሰዉዬ ግን የቸኮለ ይመስላል።ለሰላምታም ብዙ አልተጨነቀም።«ስማ ፀጋዬ ነገ ጠዋት ትልቅ ነገር ስለሚኖር ከቤተ-መንግስት ወይም ከቦሌ አካባቢ እንዳትጠፋ።» እንደቸኮለ ተናግሮ እንደቸኮለ ስልኩን ዘጋ።ጋዜጠኛዉ ሲከነክነዉ አድሮ፣ እንደከነከነዉ ሁለቱን ሥፍራዎች ከሚያማክል ቦታ አድፍጦ ይጠብቅ ያዘ።ከቀኑ አምስት ግድም።አንዲት ሞተር ብስክሊት ዉልብ አለች።መኪና ተከተላት።መኪናዋን ሌላ መኪና።ሌላዋን መኪና ሌላ ሞተር ብስክሌት።ጋዜጠኛዉ አንጋጥሶ ሲመለከት ከሁለቱ መኪኖች አንደኛዋ ዉስጥ ሰዉዬዉን አያቸዉ።ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርም።ጊዜ አላጠፋም።ናይሮቢ ደወለ ሮይተር ቢሮ።

87 ዓመቱ ነዉ።አንቱ ሥለዉ ግን።«ጋዜጠኛ አንቱ-----» አለኝ።ጋዜጠኛ ፀጋዬ ታደሰ የዛሬ እንግዳችን ነዉ።አብራችሁን ቆዩ።----አስር ዓመት በእንግሊዝኛ፣ ታሪክና ጂኦግራፊ አስተማሪነት።በማስተማሩ መኻል ግን መጫጫር ጀመረ።ዘገባ ብጤ።-------ፀጋዬ የስምንት ልጆች አባት ነዉ።የብዙ የልጅ ልጆች አያት።---ከአርባ ዓመት በላይ በጋዜጠኝኘት እንዲሕ ኖረ።ሥራና ሕይወቱን የሚዳስስ መፅሐፍ በቅርቡ እንደሚያሳትም ነግሮኛል።ለጋሽ ፀጋዬ መላካሙን ሁሉ እመኛለሁ።ነጋሽ መሐመድ ነኝ።መልካም የሳምንት መጨረሻ።

Tsegaye Tadesse Journalist  Äthiopien
ምስል privat

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ