1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጃፓን የአቶም ኃይል ጉዳት

ሰኞ፣ መጋቢት 5 2003

ባለፈው አርብ ጃፓንን የመታው ከባድ የመሬት ነውጥ በፉኩሽማው የአቶም ኃይል ማመንጫ ላይ ያደረሰው ጉዳትና መዘዙ አነጋግሮ ሳያበቃ በአካባቢውን ዛሬ የደረሰው ሌላ የመሬት ንዝረት ተጨማሪ ጉዳት አስከትሏል ።

https://p.dw.com/p/R95y
የአቶም ኃይል ማመንጫምስል AP
ንዝረቱን ተከትሎ በፉኩሽማ ቁጥር 3 የአቶም ኃይል አመንጪ አውታር ውስጥ ፍንዳታ ሲደርስ ወታደሮችን ጨምሮ 11 ሰዎችም ተጎድተዋል ። የአቶም ኃይል ማመንጫውን የሚያስተዳድረው የቶክዮ የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን እንዳስታወቀው የመሬት ንዝረቱ በተከሰተ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በኃይል ማመንጫው የሀይድሮጂን ጋዝ ፈንድቷል ። በዚሁ ማመንጫ የደረሰ ሁለተኛ ፍንዳታም የአንዱን የአቶም ማመንጫ አውታር አካል ከጥቅም ውጭ አድርጓል ።፡በርካታ ነዋሪዎች ከአካባቢው እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን እዚያ የሚቆዩትም ከቤታቸው እንዳይወጡ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ። ሂሩት መለሰ ነጋሽ መሐመድ