1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን፣ የጎርፍ አደጋና የሜርክል ጉብኝት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 27 2005

የፖለቲካ ተንታኞች ግን የሜርክልን ጉብኝትና የልገሳ ቃል በመጪዉ መስከረም ለሚደረገዉ ምርጫ እንደምረጡኝ ዘመቻ ነዉ የቆጠሩት

https://p.dw.com/p/18jZQ
Bundeskanzlerin Angela Merkel (CDU) geht am 04.06.2013 durch die Altstadt von Passau (Bayern) und spricht mit Helfern vom THW. Foto: Andreas Gebert/dpa
ምስል picture-alliance/dpa

የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት ወይዘሮ አንጌላ ሜርክል ሰሞኖን በጎርፍ የተጥለቀለቁትን የደቡብ-ምሥራቅ ጀርመን አካካቢዎችን እየተዘዋወሩ ጎበኙ።በጎርፉ ለተጎዱት ሰዎችም መንግሥታቸዉ የአንድ መቶ ሚሊዮን ዩሮ ርዳታ እንደሚሰጥ ቃል ገብተዋል።ሜርክል አደጋ የደረሰባቸዉን አካባቢዎች መጎብኘታቸዉና ርዳታ ለመስጠት ቃል መግባታቸዉ እንደ መራሒተ-መግሥት የሚጠበቅባቸዉ ሥራና ሐላፊነት በመሆኑ ሌላ ትርጉም አይሰጠዉም ባዮች አልጠፉም።የፖለቲካ ተንታኞች ግን የሜርክልን ጉብኝትና የልገሳ ቃል በመጪዉ መስከረም ለሚደረገዉ ምርጫ እንደምረጡኝ ዘመቻ ነዉ የቆጠሩት።የበርሉኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለሚካኤልን ሥለ ጉዳዩ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ይልማ ሐይለሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ