1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን ሙንስተር፦በተሽከርካሪ ጥቃት እግረኞች ተገደሉ

ቅዳሜ፣ መጋቢት 29 2010

በምዕራብ ጀርመን ሙንስተር ከተማ የእግረኛ መንገድ ላይ የወጣ ተሽከርካሪ ዛሬ ቢያንስ አራት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች እንደቆሰሉ ፖሊስ አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/2vekO
Deutschland Polizei: Täter von Münster ist tot
ምስል picture alliance/dpa

በምዕራብ ጀርመን ሙንስተር ከተማ የእግረኛ መንገድ ላይ የወጣ ተሽከርካሪ ዛሬ በርካቶችን እንደገደለ እና እንዳቆሰለ ፖሊስ አስታወቀ። ፖሊስ ቢያንስ 30 ሰዎች መቁሰላቸውን እና የጭነት መኪናው አሽከርካሪ ሕይወቱን ማጥፋቱን ገልጿል። የደረሰው ጥቃት የሽብር ጥቃት ይሁን አይሁን ፖሊስ በማጣራት ላይ ይገኛል።እንዲሁም ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎችን በመፈለግ ላይ ነው። ከሁለት ሰዓት ገደማ በፊት ወደ እግረኞች መንገድ ዘልቆ የገባው ተሽከርካሪ ውስጥ ፈንጂ መገኘቱ ተዘግቧል። የተለያዩ የዜና ምንጮች በጥቃቱ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ አራት እንደሆኑ በመዘገብ ላይ ይገኛሉ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

ልደት አበበ