1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን ለኢትዮጵያ 352 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ ሰጠች

ሰኞ፣ ኅዳር 22 2012

ጀርመን የኢትዮጵያን የምጣኔ-ሐብት ማሻሻያዎች ለመደገፍ 352.5 ሚሊዮን ዩሮ  ($388 ሚሊዮን) የገንዘብ ድጋፍ ሰጠች። የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ለማጠናከር የኢትዮጵያ የፋይናንስ ምኒስትር አሕመድ ሽዴ እና የጀርመን የኤኮኖሚ ትብብር እና ልማት ምኒስትር ጌርድ ሙለር ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ስምምነት ተፈራርመዋል።

https://p.dw.com/p/3U6C8
Äthiopien Addis Abeba Ministerpräsident Abiy Ahmed Entwicklungsminister Gerd Müller
ምስል DW/Y.G. Egziabhe

መለዋወጫ የተሟላላቸው የ144 የግብርና መሣሪያዎች ርክክብ ተደርጓል

ጀርመን የኢትዮጵያን የምጣኔ-ሐብት ማሻሻያዎች ለመደገፍ 352.5 ሚሊዮን ዩሮ  ($388 ሚሊዮን) የገንዘብ ድጋፍ ሰጠች። የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ለማጠናከር የኢትዮጵያ የፋይናንስ ምኒስትር አሕመድ ሽዴ እና የጀርመን የኤኮኖሚ ትብብር እና ልማት ምኒስትር ጌርድ ሙለር ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ስምምነት ተፈራርመዋል። በፊርማው ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተገኝተዋል።

ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ «ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የግብርናን ዘዴ ለማሻሻል ይረዳ ዘንድ ድጋፍ እንዲደረግ በጠየቁት መሠረት የጀርመን መንግሥት የለገሳቸው መለዋወጫ የተሟላላቸው የ144 የግብርና መሣሪያዎችን ቁልፎች የርክክብ ሂደት በሚመለከታቸው አካላት መካከል» መፈጸሙን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። 

ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር
ኂሩት መለሰ