1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዶ/ር ወልደ መስቀል ኮስትሬ አረፉ

ሰኞ፣ ግንቦት 8 2008

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ እንዲዉለበለብ ያደረጉ አትሌቶችን ያፈሩና ለድል ያበቁ የአትሌቲክስ አሰልጣኝ ዶክተር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

https://p.dw.com/p/1IokE
Monaco Woldemeskel Kostre Bester Trainer des Jahres 2006
ምስል Getty Images/AFP/V. Hache

[No title]

ዶ/ር ወልደ መስቀል በጎርጎሮሳዊዉ 1972 በጀርመን የሙኒክ ኦሎምፒክ ላይ የተሳተፈዉ የኢትዮጵያ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ለነበሩት ንጉሤ ሮባ ምክትል አሰልጣኝ በመሆን ነበር፤ ወደ አሰልጣኝነቱ ዓለም የገቡት። ወልደ መስቀል ኮስትሬ በጎርጎሮሳዊዉ 1982 ዓ,ም በሀንጋሪ የሁለተኛ ዲግሪያቸዉን ከተቀበሉ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በስፖርት ኮሚሽን በከፍተኛ ባለሞያነትም ሠርተዋል። ዶክተር ወልደ መስቀል ኮስትሬ በጎርጎሮሳዊዉ 1992 ዓ,ም ከተካሄደዉ ከባርሴሎና ኦሎምፒክ በዚሁ ዘመን 2008 ዓ,ም ላይ ስለከተካሄደዉ የቤጂንጉ ኦሎምፒክ ድረስ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነዉ ሲያገለግሉ ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ ስሟ ከፍ ብሎ እንዲጠራ ያደረጉትን የ5,000 እና የ10,000 ሜትር ባለድል አትሌቶች አፍርተዋል። ዶ/ር ወልደ መስቀል የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሆነዉ በተሳተፉባቸዉ አምስት የኦሎምፒክ ዉድድሮች ለኢትዮጵያ 13 የወርቅ 5 የብር እና 10 የነሐስ በድምሩ 28 ሜዳሊያዎችን ማስገኘታቸዉ ተመዝግቦላቸዋል። የዛሬ 10 ዓመት ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአትሌቲክሱ ዓለም ለአሰልጣኞች የሚሸለመውን የዓመቱ ምርጥ የአሰልጣኝነት ሽልማት አበርክቶላቸዋልም።ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኢትዮጵያዉያን ሯጮችን ለድል ያበቁ የአትሌቲክስ አሰልጣኝ ዶክተር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉን መስማቱ እንዳሳዘነዉ በድረ-ገፁ ላይ አስነብቦአል።

Allerseelen Friedhof im Herbst
ምስል picture alliance/dpa Themendienst

ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ