1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድንቅነሽ (ሉሲ) የተገኘችበት 40ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል በሊዮ

ዓርብ፣ ግንቦት 15 2006

3,2 ሚሊዮን ዓመት ያስቆጥረው የመጀመሪያቱ የሰው ዘር ምንጭ ሳትሆን እንዳልቀረች የሚነገርላት ድንቅነሽ (ሉሲ) የተባለችው ፍጡር ቅሪተ-አጽም ፤ እ ጎ አ ኅዳር 24 ቀን 1974 ዓ ም፤ አፋር ውስጥ ኀዳር በተባለ ቦታ በቁፋሮ መገኘቷ የሚታወስ ነው።

https://p.dw.com/p/1C5On
ምስል Haimanot Tiruneh

ዓለምን ያስደነቀው የዝች ፍጡር ቅሪተ-አጽም፣ ከኢትዮጵያ ውጭ በዩናይትድ ስቴትስ አብያተ መዘክር ለ 6 ዓመታት ለዐውደ ርእይ ከቀረበ በኋላ በሚያዝያ ወር ማለቂያ 2005 ዓ ም ነበረ የተመለሰው። ፈረንሳይ ፣ ኢትዮጵያ ፣ የአፍሪቃ ቀንድ የተሰኘ ማሕበር፤ ድንቅነሽ (ሉሲ) የተገኘችበትን 40ኛ ዓመት ፤ ከወዲሁ ፈረንሳይ ውስጥ ፣ በሊዮ ከተማ በልዩ ዝግጅት አክብሯል ። በስብሰባው ጥናታዊ ጽሑፎችም መቅረባቸው ታውቋል በክብረ-በዓሉ ተግኝታ የነበረችው ሃይማኖት ጥሩነህ ተከታዩን ዘገባ ልካልናለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ