ድርቅና የእርዳታ ጥሪ
ሰኞ፣ መጋቢት 12 2008ማስታወቂያ
። የሀገሪቱ መንግሥትም ከፍተኛ ገንዘብ ለዚሁ ተግባር መመደቡን አስታዉቋል። ከለጋሾች በድርቁ የተጎዱትን ለመርዳት ከፍተኛ የገንዘብ እርዳታ ያቀረበችዉ ዩናይትድ ስቴት ስትሆን የሀገሪቱ የዉጭ አስቸኳይ የእርዳታ ድርጅት USAID ኢትዮጵያ ዉስጥ የባለሙያዎች ቡድን አሠማርቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ከ50ዓመታት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ በተባለዉ ድርቅ የተጎዱትን ወገኖች ለመርዳት ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። የዓለም አቀፍ ለጋሾች እርዳ መዘግየቱን ያመለከተዉ የኢትዮጵያ መንግሥትም ለጋሾች አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጡ አሳስቧል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ