1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዳርፉር እና የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ ውሳኔ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 25 1999

የተመድ ጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ውዝግብ ባደቀቀው በምዕራብ ሱዳን የዳርፉር ግዛት 26,000 ሰላም አስከባሪ ወታደሮች እንዲሰማራ በአንድ ድምጽ ወሰነ። በውሳኔው መሰረት፡ የተመድ እና የአፍሪቃ ኅብረት ወታደሮችና ፖሊሶች በሲቭሉ የዳርፉር ህዝብ ደህንነት ላይ ስጋት በሚደቀንበት ጊዜ የኃይል ርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ፤ ውሳኔው አጥጋቢ ነው ያሉት በተመድ የሱዳን አምባሳደር ሀገራቸው የሰላሙን ሂደት አሁኑኑ እንደምትጀምር አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/E0ag
የአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ወታደር በዳርፉር
የአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ወታደር በዳርፉርምስል AP