1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ ክብረ ወሰን ተሰበረ

እሑድ፣ ነሐሴ 22 2008

ትናንት ምሽት በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው የዲያመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በተሳተፈበት ርቀት የዓለም ወጣት አዲስ ክብረ ወሰን በመስበር እና የአመቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ጭምር አሸንፏል።

https://p.dw.com/p/1JrLJ
Frankreich Paris Leichtahtletik IAAF Diamond League 3000 Laufen Yomif Kejelcha
ምስል picture-alliance/AP Photo/M. Euler

ዮሚፍ በሪዮ ኦሎምፒክ በተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ውስጥ አልተካተተም ነበር። በሌላ በኩል በዲያመንድ ሊግ በነጥብ እየመሩ ከሚገኙ አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው ሙክታር ኢድሪስ በሪዮ ኦሎምፒክስ ከ5000 ውድድር ፍፃሜ በኋላ ውጤቱ መሰረዙን ተከትሎ የደረሰበት ስነልቦናዊ ጉዳት በትናንቱ ውጤቱ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠሩን ለዶይቸ ቬለ ገልጿል።

ሐይማኖት ጥሩነህ

ልደት አበበ